ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መርቀው የከፈቱት የድሬዳዋ ኢንዱስትሩ ፓርክ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ነው ተብሏል።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለ1 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ ተገልጿል።

ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል ነው የተባለው።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ 15 ሼዶች ሲኖሩት÷ በአልባሳት እና ጨርቃጨርቅ ምርት ላይ የተሠማሩ አራት ኩባንያዎች ሥራ መጀመራቸውም ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ150 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል ።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply