ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የግማሸ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና እየመሩ ነው

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የግማሸ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና እየመሩ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚያካሂደውንና በዓመታዊ ዕቅድ መሠረት የተካሄደውን የግማሸ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና በመምራት ላይ ይገኛሉ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምዘና እየተካሄደ የሚገኘው 2013 ዓ.ም. መጋመሱን ተከትሎ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጸደቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቀጣይነት ያለውን ምዘና መካሄዱ ክፍተቶችን በመሙላት እና አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል፡፡

እንዲሁም ለዜጎች ተገቢው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ እንደሚያስችልም በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ለአንድ ቀን በሚቆይው የስራ ምዘና ሁሉም የካቢኔ አባላት እየተሳተፉ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በዕቅድ ዘመኑ ያሳኳቸውን ተግባራትና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮች በዝርዝር አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

The post ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የግማሸ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና እየመሩ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply