ጠ/ሚ ዐቢይ የሃይቅ- ቢስቲማ – ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ

ጠ/ሚ ዐቢይ የሃይቅ- ቢስቲማ – ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሃይቅ- ቢስቲማ- ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ የግንባታ ስራው የጀመረው መንገድ 74 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል።

የመንገድ ግንባታው በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ለአመታት የቆየውን የህዝብ የልማት ጥያቄ በመመለስ ለአገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተነግሯል።

የመንገድ ግንባታውን የሚያከናውኑት ፓወርኮን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና አሰር ኮንስትራክሽን በጋራ ሲሆኑ የግንባታው ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት እንደሆነ ታውቋል።

መንገዱ በአሁኑ ወቅት በጠጠር ደረጃ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የአፋርና የአማራ ክልሎችን የሚያገናኝ ነው።

የዚህ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ውል በሃምሌ ወር 2012 ዓ.ም ላይ መፈረሙ ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

The post ጠ/ሚ ዐቢይ የሃይቅ- ቢስቲማ – ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመሩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply