ጠ/ሚ ዐቢይ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በዕቅዱ መሰረት እየተካሄደ መሆኑን አስታወቁ

ጠ/ሚ ዐቢይ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በዕቅዱ መሰረት እየተካሄደ መሆኑን አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በዕቅዱ መሰረት እየተካሄደ መሆኑን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገበታ ለሃገር ፕሮጀክት አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር መወያየታቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ለፕሮጀክቶች የሚሰበሰበው ገንዘብ በዕቅዱ መሠረት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለገበታ ለገበታለሀገር የታቀደውን 3 ቢሊየን ብር ማሳካት እንደሚቻል ከአስተባባሪ ኮሚቴው ሪፖርት መረዳታቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡

ለሀገራዊ ፕሮጀክቶቹ ገንዘብ ላዋጡ ባለሀብቶች፣ ሠራተኞችና ተቋማትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የገንዘብ ማሰባሰቡን ሥራ በሁለት ሳምንት ውስጥ ለማጠናቀቅ እና ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ የገበታለሀገር መርሐ ግብርን ለማካሄድ ውሳኔ መተላለፉንም ጠቁመዋል።

The post ጠ/ሚ ዐቢይ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በዕቅዱ መሰረት እየተካሄደ መሆኑን አስታወቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply