ጣሊያን የኮሮናቫይረስ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደቦችን መጣል ጀመረች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013 ጣሊያን የኮሮናቫይረስ ስርጭት መባባሱን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደቦችን መጣል ጀመረች:: ፕሬዚዳንት ጁሴፔ ኮንቴ በሀገራቸው ዳግም የተስፋፋውን የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት ሁለተኛው ዙር የእንቅስቃሴ እቀባ እንደሚያስፈልግ በአፅንዖት ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ህዝብ በብዛት የሚስተናገድባቸውን አካባቢዎች ለደህንት ሲባል አንዲዘጉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል ነው የተባለው፡፡

ጣሊያን ይህን እምጃ ለመውሰድ የተገደደችው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቿ እንደ አዲስ በቫይረሱ መያዛቸውን የሚያሳይ ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡ቢቢሲ እንደዘገበው ከአሁን ቀደም በቫይረሱ ክፉኛ የተመታቸው ጣሊያን ከሰሞኑ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት በቫይረሱ መያዛቸው ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡

በዚህም የተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ካለፈው ውድቀታችን በመነሳት ችግሩን ፈጥነን ለመከላከል የምናባክነው ጊዜ የለንም ብለዋል፡፡ ሁሉንም ተቋማት መዝጋት ኢኮኖሚያችንን ስለሚጎዳው የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ፣ ርቀትን መጠበቅና የእጅ ንፅህናን መጠበቅ ቀዳሚዎቹ እርምጃዎች ይሆናሉ፤ለዚህም ህዝቡ ከመንግስት ጎን መቆም አለበት በማለት ጥሪ አቅርበዋል ኮንቴ፡፡ ጣሊያን በመጀመሪያው ዙር የቫይረሱ ስርጭት ከ414 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ከነዚህ መካከል ከ36 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑት ህይዎታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply