
#ጣር ላይ የሚገኘው የብልፅግና ስርዓት መንግሥት ህይወቱን ለማራዘም ዳግም የአማራውን ህዝብና የአማራውን ሃብት ንብረት መጠቀምና ማውደም ማቆም አለበት‼ ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከኮሌኔል ፈንታው መሀባና ከኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ:- የአማራን ህዝብ አንገት ለማስደፋትና ለማንበርከክ በማሰብ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጋር በጋራ በመቀናጀት ፋኖን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እናጠፋለን በሚል ቅዠት ከፍተኛ በጀት መድበው ያለ የሌለ ኃይላቸውን አሰባስበው ክልሉን የጦርነት ቀጠና ቢያደርጉትም ያሰቡት ሳይሳካ በተገላቢጦሽ ያልጠበቁት ትልቅ ኪሳራ እየደረሰባቸው መሆኑን እንደ እሬት ቢመራቸውም ሳይፈልጉ እየተጋቱት እንደሆነ እናምናለን:: በመሆንም ከበፊት ጥፋታቸው መማር ያልቻሉት እኚህ ደካማ ኃይሎች ዳግም ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ ትልቅ የጥፋት ፕሮጀክት ቀርፀው ዳግም ክልሉን እርስ በእርስ ሊያፋጁት አሲረው ጨርሰዋል:: በደምና በአጥንታቸው ውድ ህይወታቸውን ሳይሳሱ ሰጥተው ሃገርን ከመፍረስ ህዝብን ከውርደት የታደጉትን እኛ እንደ አይናችን ብሌን የምንሳሳላችውን የአማራ ህዝብ ውድ ጌጦች የሆኑትን እንደ ተርብ ተናዳፊዎች ልዩ ኃይላችንን ትልቁን ውለታውን ክደው አራክሰው አታስፈልግም ብለው ንቀውና ከጠላት ያነሰ ግምት ሰጥተው ክብሩን አዋርደው በትነው ሲያበቁ በመበተኑም ተሳልቀው ሳይጨረሱ በህዝቡና በፋኖ እንቢኝ ባይነት ከመበተን ተርፎ ዳግም ታህድሶ ብለው በማሰልጠኛ ጀግንነቱን ሰልበው ርካሽ የፖለቲካ አጀንዳቸውን አሸክመው ወንድሞቻቸው ላይ ቃታ እንዲስቡ ለማድረግና እርስ በእርስ ለማጨራረስ አቅደው እያሴሩ መሆኑ ደርሰንበታል:: ለክልሉ የፀጥታ ኃይሎች መልእክት ከኮለኔሎቹ:- የህዝብ ልጅ የሆናችሁ የልዩ ኃይል አባላትና ማሊሻዎች በሙሉ በህዝባችሁ ላይ የታወጀውን የሞት ጥሪ ከእኛ ጎን ተሰልፋችሁ ማስቆም እንኳን ባትችሉ ከጠላት ጋር አብራችሁ ወንድሞቻችሁ ላይ ለመቶኮስ ዳግም አፈ ሙዙ ወደ ህዝብና በተደጋጋሚ በሴራ እንዲወድም በተደረጉት የክልላችን ከተሞች ባለማዞር ለህዝባችን ትልቅ ውለታ እንደምትውሉለት በፅኑ እናምናለን:: በመጨረሻም በቁም በስብሶና ነቅዞ ክርፋቱን በአማራ ልጆች ውድ ህይወት ሊያጥብና ስልጣኑን ዳግም ሊያራዝም ሴራ እየጎነጎነ ያለውን ሥርዓተ መንግሥት ከስር ነቅሎ ለመጣል የሁላችንንም ርብርብ በእጅጉ ይጠይቃልና ሚሊሻውም ሆነ ተርቦቹ የልዩ ኃይል አባላት የጀመርነውን የህልውና ትግል በይፋ በመቀላቀል ህዝባችንን በጋራ ሊደርስበት ከታወጀው የሞት ቅጣት ልንጠብቀውና ከተጋረጠበት የህልውና ስጋት ዘብ ሆነን ልንታደገው እንጂ ዳግም እርስ በእርስ ጎራ ለይተን የጥይት አረር እያወረድንበት ስጋቶቹ ሁነን ልናስጨንቀው እንደማይገባ አምነን እጅ ለእጅ የምንያያዝበትና የጠላትን አንገት አስደፍተን የጦርነቱን ቀጠና ከክልላችን የምናርቅበት ወቅት መድረሱን በይፋ ማብሰር እንፈልጋለን:: ኮለኔል ፈንታ ሙሃቤ ኮለኔል ሞገስ ዘገየ https://youtu.be/bLgnerLn4oE
Source: Link to the Post