ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት” ሊዘጋጅ ነዉ ተባለ፡፡

ጣፋጭ ህይወት መልቲሚዲያ ቅን ልብ ላሳዩ ልበቀናዎች ግንቦት 30 2016 ዓ.ም የምስጋና ኘሮግራም እንደሚዘጋጅ ተነግሯል፡፡

ላለፉት ሶስት አመታት በየአመቱ ሲያዘጋጅ እንደቆየም አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡

ለአራተኛ ጊዜ “ጣፋጭ ህይወት የምስጋና ሽልማት “የተሰኘውን በሀገራችን የምስጋና ባህልን ይበልጥ ለማሳደግ የእውቅና እና የምስጋና መሰናዶ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃም ግንቦት 30 የምስጋና ቀን ሆኖ እንዲቀጥል፤ 4ተኛ ዙርም በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲከበር የተለያዮ ስራዎች እየሰሩ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

ግንቦት 30 ከጠዋት ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ የምንመሰጋገንበት ቀን ሆኖ እንደሚውልም አንስተዋል።

የተያዘውን እቅድም ለማሳካት ሁሉም ማህበረሰብ መስራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

በሀመረ ፍሬዉ

ሚያዝያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply