ጤና ሚኒስቴር ክትባት ላልጀመሩና ላቋረጡ ህፃናት የክትባት ዘመቻ አዘጋጀ።

በሀገራችን በነበሩ የተለያዮ ችግሮች ከዚህ በፊት ክትባት ጀምረው ያቋረጡና ምንም ክትባት ያልጀመሩ ህፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ የማካካሻ መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ሚኒስቴር አስታውቋል ።

የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ሰኔ 25 2016 አ.ም ጀምሮ ለ 10 ቀናት የሚቆይ እና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚሰጥ ተገልጿል ።

በተለያዮ የሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት በርካታ ህፃናት ምንም ክትባት አለመጀመራቸውንና ክትባቱን ጀምረው ማቆማቸው ተነግሯል ።

ለ10 ቀናት የሚቆየው ዘመቻ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናት ሆነው ምንም አይነት ክትማት ያልወሰዱ እና ጀምረው ያቆሙትን እንደሚያካትት ተነስቷል።

በማካካሻ መርሀ ግብሩ ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል ።

የተለያዮ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው አካባቢዎች ቅድሚያ ከሚያገኙት መካከል መሆናቸውን ሰምተናል።

አገልግሎቱን ለመስጠትም ላለፉት 2 እና 3 ወራት በቂ ዝግጅቶች መደረጋቸው ተገልጿል።

በዚህም ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ እና ሁሉም አይነት ክትባቶች እንደሚሰጡ ተጠቅሷል ።

የክትባት ዘመቻውን ተፈፃሚ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸው መወጣት አለባቸው ተብሏል ።

ወላጆችም ከ5 አመት በታች የሆኑ ክትባት ያልጀመሩ እና ጀምረው ያቆሙ ህፃን ልጆቻቸውን ወደ ህክምና ተቋም በመውሰድ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯል።

በሀመረ ፍሬዉ

ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply