ጤና ፈርስት የተሰኝ ታካሚዎች በቀጥታ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት መተግበርያ ይፋ ተደረገ፡፡አሃዱ ዌብ የተሰኝው በማማከር አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ የሚገኝው ድርጅት ጤና ፈርስት የተሰኝ…

ጤና ፈርስት የተሰኝ ታካሚዎች በቀጥታ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት መተግበርያ ይፋ ተደረገ፡፡

አሃዱ ዌብ የተሰኝው በማማከር አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ የሚገኝው ድርጅት ጤና ፈርስት የተሰኝ መተግበርያ አስተዋውቋል፡፡

ይህ መተግበርያ አዲስ እና በቀጥታ በስልክ የዶክተሮች ምክር ለማግኝት የሚረዳ እና  የህክምና አገልግሎት ለማግኝት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

አገልግሎት ፈላፊዎች በቦታ እና በጊዜ ሳይገደቡ በቀላሉ በኦላይን የህክምናና የምክር አገልግሎት የሚያገኙበት መሆኑ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሃም አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ይህ መተግበርያ ለማበልጸግ አስር ወራቶች ያህል እንደፈጀባቸውም አቶ አብርሃም ተናግረዋል፡፡

ታካሚዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በመተግበርያው በተቀመጡት ህክምና ባለሙያዎች የድምጽ የምክር አገልግሎት ማግኝት እንደሚችሉም ነው የተናገሩት፡፡

የምክር ወይም የህክምና አገልግሎት ፈላጊዎች ዶክተሮቹ በቀጠሯቸውየጤና ማዕከላት በመሄድ ሙሉ የጤና አገልግሎት ማግኝት እንደሚችሉም ተገልጻል፡፡
በጤና ፈርስት ሁሉም ሃኪሞች እና የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ ያላቸው ሲሆን ብቃታቸው በምንግስት ፍቃድ እንደተሰጣቸውም ነው የተነገረው፡፡

በጤና ፈርስት መተግበርያ አሁን ላይ 150 ያህል ይህክምና ባለሙያዎች መኖራቸው አቶ አብርሃም ነግረውናል፡፡

በዚህ መተግበርያ ከ120 በላይ የህክምና አይነቶች የምክር እና የህክምና አገልግሎት ይሰጥባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply