
“ጤንነትን ለመጠበቅ እና ለማንነቴ እሮጣለሁ ፤ ራያ አላማጣ ወሎ ነው፤ ወሎም አማራ ነው!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የራያ አላማጣ ህዝባዊ ሩጫ እና ሌሎች ውድድሮች እየተካሄዱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 2/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለዘመናት ነፃነቱን ተገፎ ሲሸማቀቅ የቆዬው አምሳያው ወሎዬ፣ ማንነቱ አማራ ፣ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ፣ የሆነው የነስበር ፣ የእነ አይበገሬው ሀገር ራያ ሀምሌ 2/2015 በማለዳው ተነስቶ በአንድነት ድምጽ ማሰማቱን በስፖርታዊ ውድድር ጀምሯል። የራያ አማራ ሀምሌ 2/2015 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። “ጤንነትን ለመጠበቅና ለማንነቴ እሮጣለሁ ፤ራያ አላማጣ ወሎ ነው፤ ወሎም አማራ ነው!” በሚል መሪ ቃል የ12 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በአላማጣ ከተማ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይ የእግር ኳስ ውድድርና የገመድ ጉተታ መርሀ ግብር ይካሄዳል ተብሏል። መረጃው_ የሰሜን ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።
Source: Link to the Post