ጤግሮስ ትሬዲንግ ከፍኖት ሃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባባር ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለ11 መምህራን አስረክበዋል።የጤግሮስ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/vieMHCtoVY2YgaIlVrw5QnaghDCYpOvoLnyKefJle9OXEpZgImkQW4HKy19Bb_dnuoPrPLZ0XUFccFUkmyB_yCLZubiJ-FKWXzNkhGvYWnVtyCG0prp6UdFADet2jBVN-SKYXpB1JZrOxEqqU98nAuezvlIxIMIIFmSlUuLrLD9HxJhL0gs5P9hBJY9utoc_YNbC8yq4Pm2eZUHK6hrtbzJ8tnz44txwB-ovEqScye7iBfDjgEsJ2N1F4TtjVnTBeCiGCYK9wEbZ_NuKD9Qw-r3WQFEmjgWFxwPmV4cOHKxdYPBwbNHBVIlQx9aO6Yx8fMMJeg6yeqqeYe-2gnmb9A.jpg

ጤግሮስ ትሬዲንግ ከፍኖት ሃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባባር ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለ11 መምህራን አስረክበዋል።

የጤግሮስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሐኔ ጌታቸው የአባልነት መስፈርታቸውን ላሟሉ እና ቁጠባቸውን ለአጠናቀቁ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች በመጀመሪያ ዙር 11 ዘመናዊ የኤሌትሪክ መኪኖችን ለ 11 መምህራን በዛሬው ዕለት ማስረከቡን ተናግረዋል።

እነዚህ ዘመናዊ የኤሌትሪክ መኪኖች የተገጣጠሙት በበላይነህ ክንዴ ጀነራል ትሬዲንግ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ብርሐኔ እንዳሉት በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞች በተደረገው ምዝገባ ከ2500 በላይ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች የኤሌክትሪክ መኪና በብድር ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም ድርጂቱ ለጤና ባለሙያዎች ፣ ለመገናኛ ብዙሃን እና ለኪነጥበብ ባለሙያዎችን የመኪና እና የቤት አቅርቦትን በብድር ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በልዑል ወልዴ

የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply