ጥምቀትን በባህርዳር በታሪካዊ ቦታው፣ ጣና ዳር ሀይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በማክበር ቱሪዝምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2015…

ጥምቀትን በባህርዳር በታሪካዊ ቦታው፣ ጣና ዳር ሀይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በማክበር ቱሪዝምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥርን በባህርዳር ከታህሳስ 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከሚከበሩ ዋና ዋና ሁነቶች መካከል በተባበሩት መንግስታት የቅርስና የባህል ተቋም በባህልና በቅርስነት እንዲሁም በሀይማኖታዊ ስርዓቱ የዓለም ሀብት ሆኖ የተመዘገበው የእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አንዱ ነው። በባህርዳር ከተማ የጥምቀት በዓል ከሀይማኖታዊ በዓል በላይ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር የሚያስችል አንድ ሁነት እንዲሆን በልዩ ትኩረት የማልማት ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጧል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የባህርዳር ሀገር ስብከት የጥምቀት በዓልን በድምቀት ማክበር የሚያስችል በጣና ዳር ቦታ በማዘጋጀት ከዚህ ዓመት ጀምሮ በዓሉን ወደ ታሪካዊ እና ሀይማኖታዊ አስተምህሮ ለመመለስ አቅዶ በመስራትና የዝግጅት ሥራውንም በማጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል። በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ በሙሉ ወደተሟላ ሥራ ይገባል የተባለው ከዓመታዊ በዓል ወጭ ዓመቱን ሙሉ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የሚሆነው የበዓሉ ማክበሪያ የቦታ ልማት ዲዛይን ተጠናቋል ተብሏል። የባህር ዳር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን እንዳጋራው። ዱዛይኑም በምስል ተመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply