#ጥሪ ቀረበ! #በቡሬ ጎጃም የተጀመረው ህዝባዊ አመፅ በሁሉም ስፋራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአማራ ህዝባዊ ኃይል/ፋኖ/ ጥሪ አቀረበ። ዛሬ ማለዳ ጀምሮ የቡሬ ወጣቶች አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ባስ…

#ጥሪ ቀረበ! #በቡሬ ጎጃም የተጀመረው ህዝባዊ አመፅ በሁሉም ስፋራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአማራ ህዝባዊ ኃይል/ፋኖ/ ጥሪ አቀረበ። ዛሬ ማለዳ ጀምሮ የቡሬ ወጣቶች አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ባስቸኳይ እንዲፈታ የሚጠይቅ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። በተጨማሪም በየጊዜው በወለጋ የሚታረዱ አማሮች እጅግ ቁጭት ውስጥ እንደከተታቸው በሰልፉ ገልፀዋል። አሁን ያለው ገዥ ስርዓት ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ በሰልፉ ተጠይቋል። በቀጣይ በተለያዮ የአማራ ከተሞች ህዝብዊ እንቢተኝነቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎ ይታሰባል። በትናንትናው ዕለት ሻለቃ መሳፍንት ተስፉ አርበኛው ባስቸኳይ እንዲፈታ መጠየቃቸው ይታወሳል። የተለያዮ ተዋቂ ሰዎች እና አርቲስቶችም አርበኛ ዘመነ ካሴን እየጎበኙት ይገኛል። “#ዘመነ ካሴ ጀግናችን ነው” “#እኔም ዘመነ ካሴ ነኝ።” “#በወለጋ የሚታረዱ አማሮች ደም፣የኛ ደም ነው።” “#ገዥው ስርዓት ለህዝብ ስልጣን ያስረክብ።” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ህዝባዊ እምቢተኝነቱ በሁሉም ስፍራ ሊቀጥል ይገባዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply