ጥቁር አሜሪካዊውን በጥይት የመታው ነጭ የአሜሪካ ፖሊስ ክስ አይመሰረትበትም መባሉ እያነጋገረ ነው ፡፡

በዊስኮንሲን ግዛት ኬኖሽ ከተማ ውስጥ ፖሊስ በሶስት ልጆች ፊት በሰባት ጥይት ተመትቶ የተረፈው ጀኮብ ብሎክ በጠበቃው በኩል ፍትህ እንዲሰጠው መጠየቁ ተገልጿል፡፡

የአካባቢው አቃቢ ህግ ድርጊቱን በፈፀመው ፖሊስ ላይ ክስ አይመሰረትም ማለቱን ተከትሎ፤ የጀኮብ ጠበቃ አሜሪካ ሶስት የፍትህ ስርዐት ነው ያላት ሲሉ ለሚዲያ አካላት አስተያየት መስጠታቸው ተነግሯል፡፡ህጉም እንዱ ለነጭ ፖሊሶች፤ አንዱ ለተወላጆች እና የመጨረሻው ለጥቁሮች የሚሰጥ ህግ ነው ማለቱ ገልጿል፡፡

የፖሊስ መኮንኑ ጠበቃ ብሬንዳን ማታው እንዳሉት ጀኮብ የስለት መሳሪያ ይዞ ወደ የተኮሰበት ፖሊስ ሰንዝሮ ነበር፤ ለዚህም ነው ደንበኛዬ ለመተኮስ የተገደደው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

******************************************************************

ቀን 30/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply