ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ራስ ገዝ ሆስፒታል ሊሆን ነው፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር ከሚገኙ አምስት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነዉን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን ራስ ገዝ የ…

ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ራስ ገዝ ሆስፒታል ሊሆን ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር ከሚገኙ አምስት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነዉን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን ራስ ገዝ የማድረግ ሂደት መጀመሩን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የጤና ሚንስቴር ዲኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን ራስ ገዝ የማድረግ ስራ ተጀምሯል፡፡

ትልልቅ የሆኑ የመንግስት ሆስፒታሎች ላይ ያለዉ የስርዓት ችግር ላይ ያተኮረ የመልሶ ማቋቋም ስራ ከተጀመረ አንድ ዓመት እንዳለፈዉ የገለጹት ሚኒስትር ድኤታዉ፤ የተቋማቱን የመረጃ ስርዓት ከማዘመን ባለፈ፣የህብረተሰቡን ጥያቄ በመመለስ ተገልጋይ ተኮር ሆነዉ እንዲሰሩ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አንዱ መሆኑን አንስተዉ ፤ ይህ እድሜ ጠገብ ተቋም ራስ ገዝ የሚሆንበት ሂደት መጀመሩን ነግረዉናል፡፡

ትልልቅ የሆኑ የመንግስት ሆስፒታሎች የሃብት እጥረት ፣ የግብዓት አቅርቦት ችግር አለባቸዉ ያሉት ዶ/ር አየለ፤ ይህ ቢሆንም ግን የህብረተሰቡን ጥያቄ መመለስም አስፈላጊ በመሆኑ ፤የመረጃ ስርዓቱን የማዘመን እና ስርዓቶችን የመለወጥ ሂደት ጀምረናል፣ ስራዉም በከፍተኛ ፍጥነት ላይ ይገኛል ብለዉናል፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፈጠራ ስራ በታከለበት መልኩ ሌሎች የግል ተቋማት በሚያስከፍሉት መጠን ባይሆንም፣ በሚያዋጣ የህክምና ስርዓት ዉስጥ ገብቶ ራሱን በራሱ በማስተዳደር የሚዘምንበት ስርዓት ዉስጥ እንዲገባ ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡

ሂደቱ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታልም አልፎ ወደ ሌሎች ተቋማት ጋር የሚሰፋበት ስራዎች ተጀምሯል ሲሉም አክለዋል፡፡

የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጤና ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ስር ሆኖ ራስ ገዝ የመሆን ሂደቱን እንደሚቀጥልም ለማወቅ ችለናል፡፡

ወደ 4.3 ሚሊዮን ብር ከሕዝብ ተዋጥቶ የተሠራው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ከተቋቋመ ከስድስት ዓሥርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ሕሙማን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply