‹‹ጥቁር እንግዳ ቤቱን ይመራል!!!› ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር››

የመለስ ዜናዊ መካነመቃብር በወታደሮች ይጠበቃል፣ ኢንጅነር ሰመኘው በቀለ ጠባቂ ሳይኖረው በወያኔ የቀን ጅቦች በግፍ ተገደለ!!!

ኢንጅነር ሰመኘው በቀለ፣  በታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ የራሱን አሻራ ያኖረ መሃንዲስ ነው፣ በስባት ዓመታት አኩሪ የሥራ ክንውነኖቹ ጉዞና እውነታዎች፣ ከመጋቢት 24 ቀን 2003 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም፣ የሚያመነጨው የሃይል መጠን 6 ሺ 450 ሜጋ ዋት፣  ለመገንባት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን 80 ቢሊዮን ብር (ከ4 ቢሊን የአሜሪካ ዶላር በላይ)፣ የሃይል ማመንጫ ዩኒቶች ብዛት 16፣ እንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የሃይል መጠን ከ 375 እስከ 400 ሜጋ ዋት፣ የዋናው ግድብ ከፍታ 145 ሜትር፣ የዋናው ግድብ ርዝመት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር፣ የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር፣ ግድቡ ሚይዘው የውሃ መጠን 74 ቢሊዩን ኪዩቢክ ሜትር፣ ግድቡ የሚሸፍነው የቦታ ስፋት 1 ሺ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር፣ ሲጠናቀቅ ውሃ የሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር፣ ለግድቡ ግንባታ ከህዝብ ቃል የተገባ የገንዘብ መጠን 12 ነጥብ 8 ቢሊዩን ብር ፣ ቃል ከተገባው እስካሁን የተሰበሰበ ገንዘብ ብዛት 9 ነጥብ 6 ቢሊዩን ብር፣ ግድቡን የጎበኙ ኢትጵያውን ብዛት 250 ሺ፣ ግድቡን የጎበኙ የውጭ ሚዲያዎች ብዛት 400፣ በ2023 እኤአ 660 ሚሊዩን ዶላር በዓመት ለሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ከኤሌትሪክ ሃይል ሽያጭ ያስገኛል ተብሎ ተተንቡዩል፡፡ ግድቡ ሥራ 60 በመቶ ያህል መጠናቀቁ ተገልፆ ነበር፡፡  የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ኢንጅነር ሰመኘው በቀለ፣ ለምን ገደሉት፣ ከግድያው በስተጀርባ እነማን ይኖራሉ፣ የግድያው ሚስጢር ምንድነው፣ የሚለውን ለመፈተሸ ‹‹ ጥቁር እንግዳ ቤቱን ይመራል!!!›› አበው ይላሉና ማለትም የጉንዳኖችን መንገድ ስትከተል ቤቱን ይመራሃል፣ ከቪላው ቤት ገብቶ፣ ከተጋጠው አጥንት የተረፈ ሥጋ ድርሻቸውን ለማንሳት ገብረ ጉንዳን ከትልቁ ቤት ወደ ጉድጎዱ ሲመላለስ ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ የጉንዳኖቹን መንገድ ከተከተልክ ፍሪዳው የታረደበትን ቤት ያሳይሃል፣ የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የግድያ ሚስጢር የገብረ ጉንዳኖቹን መንገድ ስንከተል ከታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል አያጠራጥረንም፡፡

{1} በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በመከላከያ ሚኒስትር ሥር የሚገኘው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) የተለያዩ ፌሮ ብረቶች በማምረት አልሸጥ ያለውን የአስራ ሦስት ቢሊዩን ብር የሚገመት የብረት ምርት ክምችት፣ አምርቶ አልሸጥ ብሎት ለመንግስት አቤቱታ ማሰማቱ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነበር፡፡ በወያኔ ትእዛዝ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ብረቱን በግዳጅ እንዲገዛ በመደረጉ ሳሊኒ ጥራቱን ያልጠበቀ ብረት ምርት መሆኑን አቤቱታ ቢያቀርብም ሰሚ አልተገኘም፡፡ የሜቴክ ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ ነበር፡፡ ሜቴክ የመሳሰሉት የወያኔ መንግስታዊ ሞኖፖሊነት ስም የህዳሴው ግድብ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኢትዩጵያ ባቡር ኮርፖሬሽንና፣ የኢትዩጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን፣ ፕሮጀክቶች ሥራን ጠቅሎ እንዲሰራ መደረጉ ሃገሪቱን ለከፍተኛ የሙስና ምዝበራ ዳርጎል፡፡

ሜቴክ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ (Ethiopia Power Engineering Industry (EPEI) በታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ የአምስት ቢሊዩን ዩኤስ  ዶላር ፕሮጀክት ሥራ ላይ ሜቴክ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ የኤሌክትሮ ሜካኒካል የኮንትራት ሥራ መቀመጫውን ፓሪስ ካደረገው የአልሰም (Alstom SA) ካንፓኒ ስምንት ተርባይንስና ጀነሬተሮች በ250 ሚሊዩን ዩሮ (333 ሚሊዩን ዩኤስ  ዶላር) በማቅረብ ተስማምቶል ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ የድለላ ሥራ በማከናወን ከአልሰም ኮሚሽን ያገኛል፡፡ እንዲሁም መሠረቱን አሜሪካ ካደረገው ሶላር ፓኔል ማኑፋክቸር ስፓየር ኮርፖሬሽን (Spire Corp.) እና ከቻይና ፖሊ ግሩፕ ኮርፖሬሽን (China Poly Group Corp.) ጋር የኢንጅነሪንግና የማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክቶች ሥራን በማከናወንና ከነዚህ ድርጅቶች ሜቴክ በድለላ ሥራ ኮሚሽን ከፍተኛ ገንዘብ አግኝቶል፣  ሜቴክ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ በኢትዩጵያ ህዝብ ሃብትን በመቀራመት፣ ከግድቡ ሥራ ጣልቃ በመግባት በሙስና ተግባራቸው የኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ሚስጢርን በማወቁ እንደተገደለ ፈንጣቂ ምንጮች መውጣታቸውና የገዳዮቹም የሴራ ሠንሠለት ከወያኔ አመራሮች ዘንድ እንደሚደርስ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

‹‹The Ethiopian Electric Power Corp. contracted METEC to build the electro-mechanical works for the $5 billion Grand Ethiopian Renaissance Dam on the Blue Nile River in partnership with Alstom. The Paris-based company will provide eight turbines and generators for 250 million euros ($333 million) to METEC and commission the plant.››

‹‹METEC awarded Alstom a €250m ($326m) worth contract in January 2013, to supply eight 375MW Francis turbines and generators for phase 1 of the Grand Renaissance hydro power project. Alstom will also provide engineering and power plant commissioning services as part of the contract. Tratos has been awarded a contract by Salini to provide low-and high-voltage cables for the project….Two underground power houses will be situated on the river’s right and left banks downstream of the main dam. The power houses will be equipped with ten and five 375MW Francis turbine units respectively. A 500kV double bus-bar switchyard will be built 1.4km downstream of the main dam to transmit the output of the hydroelectric plant.›› ‹‹It is the main electromechanical and hydraulics steel structure contractor of the Renaissance Dam. The Corporation has provided steel products used for the work of diverting the course of the river, which was officially commissioned on May 28.››
በሜይ 17ቀን 2015 እኤአ በኢትዩጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ላይ በወጣው መረጃ መሠረት የመከላከያ ሚንስቴር፣ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን አንዱ አካል የሆነው የኢትዩጵያ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ በስሩ ሰባት ፋብሪካዎች በማቀፍ በኦሮሚያ ክልል በቡራዩ ከተማ የተገነባው ታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረጫ ፋብሪካ በ350 ሚሊዩን ብር ወጪ መነንባቱ ተገልፆል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የኢትዩጵያ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አሰፋ ዩሐንስ ለኃል ማማንጫ፣ማስተላለፍያ፣ማሰራጫና ለኃይል ቁጠባ የሚያገለግሉ ፓወር ፕላንቶችን፤ የኤሌትሪክ እቃዎችና መለዋወጫዎች፣ የዲዛይን፣ የምርትና ተከላ ስራ በመስራት ከፍተኛ ሰኬት እንዳስመዘገቡ ይገልፃሉ፡፡ ፋብሪካው 12 ሽህ የተለያዩ አቅምና መጠን ያላቸው ትራንስፎርመሮችን እንዲሁም 100 ሽህ ኪሎ ሜትር የሚሆን የተለያዩ ኬብሎችን በማምረት ለገበያ እንደሚያቀርብ ገልፀዋል፡፡ ፋብሪካውን ወደፊት ወደ ኢንድስትሪ ዞን በመቀየር ሰፋፊ የኢንደስትሪ ልማት ለማካሄድ እቅድ እንዳለ ገልፀዋል፡፡ እንደ ውኃ ማቆር፣ ፋብሪካ ማቆር በኢንድስትሪ ዞን ስም የገበሬውን መሬት መንጠቅ እየተስፋፋ የመጣ የዘመኑ በሽታ ነው፡፡ በኢትዩጵያ የግል ዘርፉን የኢኮኖሚ ተሳትፎ የነጠቀው መንግስታዊው ዘርፍ የሆነው የመከላከያ ሚንስቴር፣ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን እራሱን ለገበያ ውድድርና ጥናት ያላዘጋጀ በአድሎ ያለጨረታና ጥናት ስራዎች በመንግስት ሰለሚሠጠው እራሱን ለመፈተሸ ዕድል የተነፈገ ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከቻይና ከቱርክ አሮጌ ፋብሪካ ገዝቶ አገር ውስጥ በመግጠም፤ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አስረኛ ወጣን እያለ በመለፈፍ ውጪ መርፌና ምላጭ እንኮን ስርቶ አያውቅም፣  ትራንስፎርመር ገጣጠምን ነው ፈበረክን ነው የሚባለው፡፡ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን በታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ ከፍተኛ የሙስ ሥራ በመስራትና የጣልቃ ገብነት ሚና እንደነበራቸው ሙያተኞች ይገልፃሉ፡፡

{2} መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ በ1995እኤአ ከመቐለ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ፋብሪካው የተቆቆመበት የተከፈለ ካፒታል 240 ሚሊዩን ብር  ነው፡፡ የፋብሪካው ኢንቨስትመንት ካፒታል መጀመሪው መስመር 1.2 ቢሊዩን ብር እንዲሁም አዲሱ መስመር 2 ቢሊዩን ብር ወጪ ወጥቶበታል፡፡ ፋብሪካው በ2000 እኤአ ምርት ሲጀምር፣ ኦፒሲና ፕሮቲያን (OPC, protean cement) ሲሚንቶ ዓይነቶች አመረተ፡፡ መሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ የፋብሪካው ከአዲስ አበባ 770 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስለሚገኝ የሲሚንቶ ምርቶቹን በመላ ሀገሪቱ ለማከፈፈልና መሸጥ አይችልም፡፡ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ በሃገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር ለመወዳደር ባለመቻሉ የተነሳ የሲሚንቶ ምርቱን ለመሸጥ ባለመቻሉ ለኪሳራ ተዳርጎ ነበር፡፡  በዚህም ምክንያት የህወሃት መንግስት ለመንግስት ፕሮጀክቶች መስሪያ በትእዛዝ ከመሶቦ ሲሚንቶ እንዲገዙ በማድረግ ኪሳራውን በህዝብ ኃብት ኪሳራ  አሸጋሽጎል፡፡ መሶቦ ፋብሪካ የሲሚንቶ ምርቶቹን ለኢፈርት ንብረት ለሆኑት ትራንስ ኢትዩጵያና ጉና ማጎጎዥ ድርጅቶች በኩንታል 80 ብር እስከ አዲስአበባ  ድረስ ያስከፍሉ ነበር፡፡ በግዜው የግሉ ዘርፍ የትራንስፖርት የጭነት ገበያው ዋጋ ከ50 ብር በኩንታል ነበር፡፡ በህወሃት መንግስት የመሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቶች ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ፣ ቢኒ ሻንጉል ጉሙዝ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሥራ ሲሚንቶ በማመላለስ መሶቦ፣ ትራንስ ኢትዩጵያና ጉና ማጎጎዥ ድርጅቶች የጥቅሙ ተጋሪዎች ሆነዋል፡፡ ህወሓት የሚያሳዝነው በሃገር ሃብት እንዲህ መጠቃቀምና በኪሳራ ኢንቨስትመንት ስራዎች ሲሰሩ ምን ያህል የማህይሞች ሥራ ከመሶቦ ግድቡ ድረስ ሲሚንቶ ዋጋ በላይ የነዳጅ ወጪው ከፍተኛ መሆኑ እየታወቀ በሃገር ኃብት ላይና በታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ወጪ በመጨመሩ ሃገሪቱን ለኪሳራ  የደረገ የወያኔ አመራር ለግል ጥቅም ሲሉ  የመሰቦ የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ትራንስ ኢትዩጵያና ጉና ማጎጎዥ ድርጅቶች ከፍተኛ የጥቅም ተቆዳሽ በመሆን የሙስናው ሠንሠለት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ ታሪክ አንድ ቀን ይፋ ያወጣዋል እንላለን፡፡  የእነዚህን ድርጅቶች ሚስጢር ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በማወቁ  እንደተገደለ ፈንጣቂ ምንጮች መውጣታቸውና የገዳዮቹም የሴራ ሠንሠለት ከወያኔ አመራሮች ዘንድ እንደሚደርስ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

 

{3} መስፍን ኢንጅነሪንግ MESFIN  Engineering  በታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ የከፊል የኮንትራት ሥራ ከሜቴክ በመቀበል ብቃት የሌለው ስራ በመስራት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል እንደፈፀሙ ሙያተኞች ይገልፃሉ፡፡ በተመሳሳይ መስፍን ኢንጅነሪንግ ሦስት ቢሊዮን ብር ኮንትራት ሥራ ከጣና በለስ ስኮር ፋብሪካ እንተሰጠው የቅርብ  ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

{4} ወይዘሮ አኢኮ ሥዩም፣ የኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ወይዘሮ አኢኮ ሥዩም ባለቤት/ የሙስና ኮማሪት! አዜቡ መስፍን እህት/ በደቡብ ሱዳን ውስጥ በጄነራል ፃድቃን ገብረትንሣይ በተመቻቸላት የሽርክና ንግድ በደቡብ ሱዳን በኮንስትራክሽን በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ እንዲሁም የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በማቅረብ የደለበ የዶላር ኃብት ከምድረ-ደቡብ ሱዳን እንደዘረፉ ውስጥ ሃገር ወዳድ የትግራይ ልጆች አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ኦርኪድ በሃገር ውስጥ በከባድ ጭነት ማመላለሻ ኩባንያው  የመሶቦ ሲሚንቶን ምርት ለህዳሴው ግድብ ሥራ በማቅረብና በማጎጎዝ ዘርፍ የትግራይን ህዝብ የመዘበረ የንግድ ተቆም ነው፡፡ ኦርኪድ በመንገድ ኮንስትራክሽን ኩባንያው በብዙ ቢሊዩን ብር ፕሮጀክቶችን በመገንባትና በመሠረት ቁፋሮ ግንባታ ሥራ ኩባንያም አለው፡፡ በፎርብስ በተባለው መፅሄት ዓመታዊ ገቢያቸው ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳላቸው ይፋ ሆኖል፡፡  የኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ በታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ ያለጨረታና ውድድር  ሥራ የተሰጠው ድርጅት ሚስጢርን ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በማወቁ  እንደተገደለ ፈንጣቂ ምንጮች መውጣታቸውና የገዳዮቹም የሴራ ሠንሠለት ከወያኔ አመራሮች ዘንድ እንደሚደርስ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡

 

{5} ሳሊኒ ኢምፕሬጂሎ ኮንስትራክሽን፣ (Salini Costruttori) የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም 6000 ሜጋ ዋት፣ የፕሮጀክቱ ወጪ 4.1 ቢሊዩን ዶለር ወይም (74,538,000,000 ቢሊዩን ብር) አጠቃላይ የግንባታው ወጪ ሽፋን ድርሻ፣ ኮንትራክተር ሳሊኒ ኢምፕሬጂሎ ኮንስትራክሽን(ሃገረ- ጣልያን) እየተገነባ ያለ ነው፡፡ “The planning and implementation of this project has all been decided behind closed doors. Its $4.8 billion contract was awarded without competitive bidding, for example, to Salini Costruttori, an Italian firm favoured by the ruling party; Salini is also building the controversial Gibe III Dam on Ethiopia’s Omo River.” የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት፣ በአፕሪል 27/2013 ቻይና ለኢትዬጵያ ዩኤስ 1 ቢሊዩን ዶለር (18,180,000,000 ቢሊዩን ብር) ብድር ሰጠች፡፡ ብድሩም ከአዲስ አበባ ወደ ህዳሴ ግድብ የኤሊትሪክ መስመር ዝርጋታ ለማገናኘት  እንደሆነ ተገልፆል፡፡ የህዳሴው ግድብ የፕሮጀክት ውጪ ዩኤስ 4.1 ቢሊዩን ዶለር ወይም (74,538,000,000  ቢሊዩን ብር) ተገምቶ ነበር፡፡ በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገነባ ግድብ ሲሆን 6450 ሜጋዋት የሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ያመነጫል ተብሎ ይገመታል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በ4.8 ቢሊዩን ዶለር ያለ አንዳች ዓለም ዓቀፍ ጨረታ ውድድር ለጣሊያኑ ካንፓኒ ለሳሊኒ ኮንስትሩቶሪ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ተሰጠ፡፡ ሳሊኒ የግልገል ጊቤ 3 ግድብ ፣በኦሞ ወንዝ ላይ መገንባቱ ይታወቃል፡፡ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ሃገሪቱ ከኢነርጂና ኃይል ሽያጭ በ2023 እኤአ ለኢትዩጵያ በአመት አንድ ቢሊዩን ዶለር ወደ ውጭ ሃገር ኮረንቲ በመሸጥ ገቢ እንደምታገኝ የአለም ባንክ የኢኮኖሚክስ ጠበብት አረጋርጠዋል፡፡ ይህም የታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የሃይድሮ ኤሌትሪክ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተባለው ግዜ ያለ አንዳች እንከን ከተጠናቀቀ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡ ወያኔ ሃገሪቱን በብድር ተብትቦ፣ ኢኮኖሚያዊ ኃብታችንን በእዳ በማስያዝ ሃገሪቱን ለቻይና ወለድ አግድ አስይዞና ዘርፎ በመቐለ መሽጎ የፀረ-ዴሞክራሲ ኃይሎችን በመላ ሃገሪቱ በማሰማራት የተጀመረውን ለውጥ ለማጨናገፍ ሴራ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱንና ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን እንደማይቻል የሚገነዘቡበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ ወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ስልጣኑን ካጣ ሃገሪቱን ለማበጣበጥ ለ27 አመታት የግፍ አገዛዥ በህዝብ ላይ ፈፅሞል፡፡

{5} የቻይና መንግስት በኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ዘርፍ ተሳትፎን በተመለከተ የቻይና መንግስት በኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል በማመንጨት፣ኃይል በማከፋፈልና  ዓለም ዓቀፍዊ የኃይል አቅርቦት የማመቻቸት ፕሮግራም ዘርፍ ተሳትፎው ከአለፈው አስር አመታት ጀምሮ እያደገ መጥቶል፡፡ ከሠንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው የቻይና ካንፓኒዎች በሁሉም የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጣሊያንያዊ  ከሆነው ሳሊኒ ካንፓኒ ከሚሰራው የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት  በስተቀር ማለት ይቻላል፡፡ የቻይና ካንፓኒዎች በሁሉም የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ያገኙት አጠቃላይ የኮንትራት ዋጋ 1.7 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ይገመታል፡፡ የቻይና ካንፓኒዎች ከኃይል ማመንጫ ማከፋፈያ ፕሮጀክቶች 350 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለርና ከመንግስታቶች ዓለም ዓቀፍዊ የኃይል አቅርቦት የማመቻቸት ፕሮግራም 23 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር አግኝተዋል፡፡

 

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (2008-2012) ኢትዮጵያ  814 ወደ 4100 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ላይ ደርሶል፡፡ የኢሌትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሃላፊ የነበሩት ኢንጅነር ምህረት ደበበ የኤልፓ የቦርድ አባል የነበሩት ዶክተር ደብረፅዮንና የሜቴክ ጀነራል ክንፈ ዳኘው በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ ጣልቃ በመግባትና ከሜቴክ ጋር የጥቅም ግጭት ይፈጥራል በማለት ተቃውሞቸውን ባሰሙ ጊዜ  ኢንጅነር ምህረት ደበበ ከስላጣናቸው በማንሳት ኢንጅነር አዜብን መተካታቸው በስራ ባልደረቦቻቸው ይፋ ሆኖል፡፡ የሜቴክ ጀነራል ክንፈ ዳኘው በግድቡ ሥራ ከፍተኛ ገንዘብ ያባከኑና የገቡትን የኮንትራት ሥራ ሳይሰሩ ለመስፍን ኢንጅነሪንግ የስብ ኮንትራት ስራ የእሰጡ ሥራውን ያጎትቱ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የኢሌትሪክ ኃይል ፕሮጀክት የኤሌትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅምን በ2007 ከነበረበት 2,220.5 ሜጋ ዋት በ2012 ወደ 17,347 ሜጋ ዋት ከፍ ለማድረግ ግብ ተጥሎል፡፡ በሃገሪቱ የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥና ችግር እስካሁን መፍትሄ አላገኘም፣በሃገሪቱ ያሉ ፍብሪካዎች ከፍተኛ ምርት ለማምረት ያልቻሉት በኤሌትሪክ ኃይል  አቅርቦት ችግር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ታላቁ የኢትዩጵያ የህዳሴ ግድብ፣ ከኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት 636 ሚሊዩን ዶላር ገቢ እንደሚገኝ መንግስት በምናባዊ አኃዞቹ ገልፆል፡፡ ግድቡ ሲያልቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር እንደሚቀረፍ፣ ድህነት እንደሚወገድ፣በቀን ሦስቴ እንደምንበላ፣ ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች እንደምንዘል ወዘተ የተገባው ቃል ኪዳን ከአምስት አመት በኃላ፣ በ2012 እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር፣ 636  ሚሊዩን ዶላር ገቢ ብቻ እንደምናገኝ ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ይሄስ ቁጥር እውነት ይሆናል ብሎ የሚጠብቅ ካለ ይሳሳታል ግድቡ በታባለው ግዜ ያልቃል ወይ፣ ግድቡ ከ2003 ተጀምሮ 2007 ይጠናቀቃል ተብሎ አላለቀም፡፡ እንደ ዓለም ባንክ ጥናታዊ ግምት  ግድቡ በ2023 እኤአ (2016እኢአ) በታቀደው መሠረት ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ፣ ዓመታዊው የግድቡ ውኃ የመያዝ አቅምና መጠን ከጨመረና ሌሎች ችግሮች ካላጋጠሙት ኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር ከኤሌትሪክ ኃይል ሽያጭ ገቢ ታገኛለች ይላል ሙለር፡፡ የዓለም ባንክ ጥናት መሠረት ሃገሪቱ  1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች እያለ፣ ወያኔ ደግሞ ከኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት 636 ሚሊዩን ዶላር ገቢ እናገኛለን ይላል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ገቢውን ያሳነሱበት ምክንያት ቀሪውን 364 ሚሊዮን ዶላር ለመዝረፍ የታለመ ነው፡፡ መረጃውን ከድረ-ገፁ ያንቡ፡-

Ethiopia’s Renaissance Dam – A mega dam with potentially mega consequences/By Haydar Yousif, ThinkAfricaPress, December 4, 2012

World Bank Urges Ethiopia to Devalue Birr to Boost Exports, By William Davison, Bloomberg July 24, 2014

“Lars Moller, the World bank’s chief economist in Ethiopia, told reporters today in the capital, Addis Ababa. Ethiopia, the world’s most populous landlocked nation, may grow as much as 8.5 percent this year and next, the International Monetary Fund said last month. The nation earns most foreign-exchange from state-owned Ethiopian Airlines, while coffee exports from Africa’s largest producer of the beans are the highest grossing commodity. The World Bank estimates Ethiopia could earn $1 billion a year from exporting electricity by 2023 if all of its hydroelectric projects are completed as planned, Moller said. ’’ To contact the reporter on this story: William Davison in Addis Ababa at [email protected] To contact the editors responsible for this story: Nasreen Seria at [email protected] Paul Richardson, Sarah McGregor, Andres R. Martinez

በዓለም ባንክ ጥናት መሠረት በ2023እኤአ ኢትዮጵያ ከኤሌትሪክ ኃይል ሽያጭ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች፡፡ እያለ፣ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በእኛ በ2016 ዓ/ም  ደግሞ ከኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት 636 ሚሊዩን ዶላር ገቢ እናገኛለን ይላል፡፡ ወያኔ ገቢውን ያሳነሱበት ምክንያት ቀሪውን 364 ሚሊዮን ዶላር ለመዝረፍ የታለመ ነው፡፡ በጥናቱ መሠረት  የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራና የግድቡ የውኃ ሙሌት  ከ2003 ተጀምሮ፣በ2016 ዓ/ም እንደሚጠናቀቅ ከጅምሩ ይታወቃል፡፡ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በ15 ዓመታት ውስጥ እንደሚያልቅ ጥናቱ ዋቢ ነው፡፡

ህዝቡ ለህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ገንዘብ እንዲያዋጣ፣ ቦንድ እንዲገዛ፣ እስክስታ እንዲወርድ፣ እንዲያቅራራ፣ እንዲሸልል  በማድረግ ይዘርፉታል፡፡ ወያኔ የፖለቲካ ስልጣኑን ካጣ አገር ይፈርሳል ይለናል፣ ወያኔ የህዳሴ ግድቡ ቦንዱን ለግብፅና ሱዳን በመሸጥ ገንዘቡን ዘርፎ ያሸሻል፣ ሃገሪቱን ለቻይናና ለውጪ አገራት ብድር ዘፍቆት ይኮበልላል፣ ለስልጣናቸው ሱስ ሲሉ ምንም ነገር ይፈፅማሉ፡፡

  1. As the sector continues to expand its access program and connect more customers from additional parts of the country, the domestic demand for electricity is expected to remain strong. The domestic demand is expected to reach nearly 9,000 GWh by end of this decade using the sector’s moderate growth forecast.
  2. Moreover, a large part of the future growth will also come from energy exports to neighboring countries. The Djibouti interconnector has already started power trading (as of 2011) and the Sudan interconnector began power trading in 2012. The Kenya interconnector is expected to being trading in 2017/2018. The combined electricity export is expected to exceed 7,000 GWh by end of this decade – the bulk of which would come from the Kenya interconnector (see table below). The international sale of power is expected to be at competitive prices (approx. US$ 0.07/kWh) which will bring significant foreign exchange revenue. Overall, it is anticipated that the   sector’s operating revenue will grow around 8-10% to US$ 200 million a year (on average) from FY2013-2016, growing to US$ 600 million FY2017-20 (after exports to Kenya start).

የኤሌትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሃገራት እየሸጠች ሲሆን በ2011እኤአ ለጅቡቲ መንግሥት የኤሌትሪክ ጅረት ቆት  መሥመር በመዘርጋት ኃይል አቅርቦት ለመሸጥ ችላላች፡፡በ2012 እኤአ ለሱዳን መንግስት የኤሌትሪክ መሥመር በመዘርጋት ኃይል አቅርቦት ለመሸጥ ችላላች፡፡ እንዲሁም በ2017/18 እኤአ ለኬንያ መንግስት የኤሌትሪክ መሥመር በመዘርጋት ኃይል አቅርቦት ለመሸጥ እቅድ አላት፡፡ አጠቃላይ  የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት 7000 ጊጋ ዋት በስዓት ለማቅረብ በዚህ አስር ዓመታት ውስጥ እቅድ አለ፡፡ ዓለም ኣቀፍ የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት ሽያጭ ተወዳዳሪ ዋጋ ዩኤስ 0.07 ኪሎዋት በሰዓት በመሆኑ ለሃገሪቱ ተቀም ያለ የውጪ ምንዛሪ ገቢ ያስገኛል፡፡ በአጠቃላይ በ2013 እስከ 2016 እኤአ የኤሌትሪክ ኃይል ሽያጭ ገቢ ከ8 አስከ 10 በመቶ የኤስ 200 ሚሊነረ ዶላር በዓመት በአማካኝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በ2017 እስከ 2020እኤአ የኬንያ የኤሌትሪክ ኃይል ሽያጭ ሲታከልበት እስከ 600 መቶ ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኛል ተብሎ ተገምቶል፡፡ ወያኔ በአመት 364 ሚሊዮን ዶላር ለመዝረፍ ያቀደውን ሚስጢር ለኢንጅነር ሰመኘው በቀለ በማወቁ ያጋልጠናል ብለው ሊገድሉት እንደሚችሉ ጥርጣሬአችንን ያሰፋዋል፡፡

 

 

የታላቁ ስመኘው የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ እውን ይሆናል!!!

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ ገዳዬችና የሰኔ 16 ቦንብ ገዳዬች በፍጥነት ለፍርድ ይቅረቡ!!! በሃገሪቱ ሰው ይሞታል ይጣራል ይባላል፣ እስካሁን ለፍርድ የቀረበ የለም!!! የዘገየ ፍርድ አንሻም!!!

መቐለ የመሸገው ፀረ-ዲሞክራቲክ የወያኔ ኃይል ሙሰኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ለፖለቲካ ሰዎቻችን ከቀን ጅቦች ግድያ ጥበቃ መንግሥት ያድርግላቸው እንላለን!!!

አፋጣኝ ፍርድ ይሰጥ!!!

ግድያ መቼም የትም አይደገም!!!

Leave a Reply