
#ጥቁር_ለመሆናችን_ተጠያቂው_አፄ_ምንሊክ_ነው። #አድዋ_የኛ_ነው_ምኒልክ_ተረት_ነው፤ #ለጋ_ትርክት የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ሁሉም ነገሮች ውለው ሲያድሩ ትናንት እየሆኑ ብዙ ትናንቶች በአምናና ሃችአምና ክምር አመታትን ወልደው ትውልዶች ሲያልፉ፤ ድርጊቶች/ሁነቶች ሁሉ በነገር ታሪክ መልኩ ይሰደራሉ። #ታሪክ:- የድርጊት/ሁነት መነሻና መድረሻ፣ ፈፃሚና አስፈፃሚ፣ ሰጭና ተቀባይ ያለው እንደመሆኑ መጠን ድርጊቱ/ሁነቱ ሲፈፀም ሆን ተብሎም ሆነ በዘፈቀደ በመቸት ሃድድ አሻራውን ጥሎ ሲያልፍ ፣ በአፈታሪክም ይሁን በሰነድ ዘመናትን ተሻግሮ ሲሄድ ወዳጅም ጠላትም አፍርቶ የራሱን ስነ ልቦናን ገንብቶ ይዘልቃል። በመሆኑም #ታሪክ ስለወደዱት የማይገዝፍ ስለጠሉት የማኮስስ በሁለቱም ወገን ቦታ ያለው ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የሚኖር የትናንት ሁነት ነው። የሆነው ሆኖ ለዛሬ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ በዚህ ዓመት በጥቁር ህዝቦች ዘንድ ለ127ኛ ጊዜ በክብርና በኩራት የሚከበረው በአለም ታሪክ፣ በተለይም በአፍሪካ ምድር ከተከናወኑ እና በሰው ልጅ የስልጣኔ ታሪክ ውስጥ /ከባሪያ ስርዓት ወደ ቅኝ ግዛት የተሸጋገሩበት/ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግዙፍ ክስተት መካከል አንዱ የሆነው #የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ነው። ፃሃፍት፣ በተለይም አለም አቀፍ ፃሃፍት በታሪክ ድርሳናታቸው ስለ #አድዋ ብዙ ያሉትና ብዙ የተባለለት ስለሆነ #አድዋ እንድህ ነው ልላችሁ አልወድም። ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ወድህ ስለ #አድዋ ሲነሳ የታሪኩን ሁነት በኩራት ተርከው አክተሩን ተቀያሪ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ የሚዳዳቸው የታሪክ አሽክላዎች ሳይ ትዝብቴን ለመግለፅ ወደድሁ። አሁን ላይ የኛዎቹ ሰዎች ዳቦ ጠብ በማያደርግና ሃገራችን ላለባት ችግር መልስ በማይሰጥ ትናንት፣ ባልሰሩት ታሪክ የታሪክ ሽሚያ ውስጥ ተጥደው #አድዋን የእኛ ነው ብለው #ምኒሊክን ተረት ለማድረግ መሞከራቸው በራሱ ሽንፈተታቸውን ተቀብለው ታሪክን ከዘገቡት ከጣሊያን ዘማቾች እና ምርኮኞች አለመሻላቸው ያሳዝናል። ትውልዳችን የስነልቦና መቀንጨር አጋጥሞታል ብየ አፌን ሞልቸ እንድናገር የሚያስችል ሃሳብ ባነሳ፣ አንድ ትውልድ ሃገር የሚጠቅም፣ ትውልድ የሚኮራበት የራሱን ታሪክ ሰርቶ ማለፍ አንድ ነገር ነው። ይህ ባይሆን እንኳ ታሪክ ሰሪዎችን እና ታሪክን እንደ ጅብ ከቦ መዘነጣጠልና ምልክቱን ወደየራሱ ጎሳ መውሰዱ ግን መቀንጨር ነው። ለምሳሌ #የሰሜኑ ሰዎች #አደዋ #ከአሉላ_አባነጋ ውጭ አይታያቸውም፣ የታችኛው አገር ሰዎች ደግሞ #ከባልቻ_አባ_ነፍሶ ውጭ ሌላው ባንዳ ተደርጎ ነው የሚሳለው፣ እንዳውም ባለፉት ሁለት አመታት በመንግስት ደረጃ ሳይቀር ክብረ በዓሉ ራሱ #ባልቻ_አባነፍሶ እና #7ኛው ንጉስ አብረው ባነር ላይ ገዝፈው በማህበራዊ ሚዲያ ሳይቀር live ሲለቀቁ ማየት ብርቅ አይደለም፣ ሌላውም ከብሄሩ አንድ የጦር አዝማች ሲያገኝ ከታሪክ ላይ በወረንጦ ነቅሎ ወደ ጎሳው በመውሰድ የአድዋን ግልባጭ ለመፍጠር ይዳዳዋል። ግን ግን የሁለም መሪና አሰማሪ፣ አዋጅ ጎሳሚና አስጎሳሚ፣ ተዋጊና አዋጊ #አፄ_ምኒልክ ከነ #ንግስታቸው እንደነበሩ እንደትስ ተብሎ ሊካድ ይችላል። የበቀልንበት መሬት ራሱ ምስክር ነው። ይህ ማለት ግን እንደ ሃገር መሪ #አፄ_ምንሊክ ይምሩት እንጅ ለጥፋትም ይሁን ለልማት ከሚንስትሮቻቸው ጀምሮ እስከ ስንቅ አቀባዮቻቸው ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ህዝብ፣ በኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍሶ፤ ስጋውን ለአሞራ ነፍሱን ለሃገሩ የሰጠ መሆንኑ ልነግራችሁ አልደፍርም፣ አያጠራጥርምና። ታድያ የዛሬው እናንተነታችሁን አምጦ የወለዳችሁን የዛን ዘመን መሪ ላይ ምን ሃሌሌ አስጨፈራችሁ? አንዳንዴ ሳስበው #ጥቁር_ለመሆናችን_ተጠያቂው_ምንሊክ_ነው፣ #እኛ_የጣሊያን_ነጮች_ነበርን አይነት ክስ የምታቀርቡ ይመስላል😂 የአሁኗ ኢትዮጵያ ሃገረ መንግስትም ሆነ ዘመናዊ ስልጣኔ የተወለደው #በአፄ_ምኒልክ ዘመን በመሆኑ #ምንሊክን መጥላት ራስን መጥላት ነው። ብታምኑም ባታምኑም እኛ #የምንሊክ ውጤቶች ነን። አሁን አሁን ትውልዱ የታሪክ ቅንብቻ ሆኗል። የራሱ ታሪክ የለውም፣ ታሪክ አይሰራም፣ ታሪክ አይፈጥርም። የዛሬዋ ኢትዮጵያ ያሉባትን የኢኮኖሚ ችግር ከመፍታት ይልቅ ጭንቅላቱ በትናንትን ተወጥሮ ትናንትን እየታገለ ሲቅበዘበዝ የሚውል ሆኗል። ሆናና መሪ ታሪኩን የሚያላምጥ ትውልድ ያበቅላልና ተነስ ሲባል የሚነሳ ተቀመጥ ሲባል የሚቀመጥ መነሻና መድረሻውን የማያውቅ “በተከበብኩ” ብቻ ያለአመንክንዮ በመንጋ የሚነጉድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፣ በተቀደደልን ቦይ መፍሰስ። እኔ በራሴ ምክንያት #አፄ_ምኒልክን አልወዳቸውም ሆኖም ግን ለጥቁር ህዝቦች፣ ለሃገር ክብር፣ አንድነት እና ነፃነት ካበረከቱት አስተዋፅዖ አንፃር ምናልባትም በታሪክም በዘመኔም ካየኋቸው /በትንሹ #ከአፄ_ቴዎድሮስ እስከ አሁኑ #7ኛው_ንጉስ/ ድረስ ከሁሉም በላይ ዘላን ህዝብን አሰባስበው፣ ሃገር የመሰረቱና ዘመናዊነትን ያስተዋወቁ ምርጥ የመሪነት አቅም የነበራቸው መሪ ስለሆኑ ለኔ ንጉሴ ናቸው፣ እኮራባቸዋለሁ። እንኳን እሳቸውን እሳቸው በሰሩት ቤት ገብቶ ስንቱም ንጉስና መሪ ተብሏል። እውነትም ይሁን ስህተት ከታሪክ ጋር መጋጨት በራስ ተወርውሮ ከግንብ ጋር እንደመላተም ነው። እስኪ እኛ ለሁላችንም ምርጥ የምንለውንና ለሁላችንም የሚሆን ለትውልድ የምናሻግረው የራሳችን መልካም ታሪክ እንስራ “የሁሉም ነገር ውጤት መሰረቱ መሪ ነው፤ ለትውልድ መበላሸትም መቃናትም ተጠያቂውም መሪው ነው።” መሪ❗️ አበቃሁ 🙏ሻሎም ለኢትዮጵያ🙏 Feisel H. Hassen “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post