ካንሰር በገዳይነታቸው ግንባር ቀደም ከሚባሉ የህመም አይነቶች መካከል አንዱ ነው።
የካንሰር ህመም በጊዜው ከተደረሰበት ሊታከም እንደሚችል የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡
በኢትዮጵያ በየአመቱ በተለያየ አይነት የካንሰር ህመም የሚጠቁ ታማሚዎች ቁጥር መበራከቱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በማቲዎስ ወንዱ ኢትዮጲያ የካንሰር ማእከል የሜዲካል ኮርድኔተር እና የካንሰር ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር ናትናኤል አለማየሁ እንደተናገሩት፤ በአለም አቀፍ ደረጃ የካንሰር ታሚዎች ቁጥር መጨመሩን ገልጸው፤ በይበልጥ በታዳጊ ሀገራት እንደሁም በሀገራችን የካንሰር ታማሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
#ለካንሰር ታማሚች ቁጥር መጨመር እንደ አጋላጭ ሁኔታ የሚጠቀሰው፤
ዶክተር ናትናኤል ለካንሰር ህሙሟን ቁጥር መጨመር የተለያዩ ጥናቶች ሊጠኑ ይገባል ያሉ ሲሆን፣ እንደ አጋላጭ ሁኔታ የሚጠቀሰው፤ የህዝብ ቁጥር መጨመር ፣ የሰዎች የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ማለትም የእግር መንገድ አለማዘውተር እና ለረጅም ሰአታት መቀመጥ እና መሰል ልማዳዊ ድርጊቶች ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡
የአመጋጋብ ሁኔታ መቀየር ( አዘውትሮ ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች አጋላጭ የሆኑ ምግቦችን መመገብ )
ከዚህ ቀደም ከነበረው የመመርመር አቅም መሻሻል የካንሰር ታማሚዎች ለመለየት መቻሉን እንደ ምክንያት ይጠቅሳሉ፡፡
-ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል
-የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር
ካንሰር እንደማንኛውም ህመም ታክሞ መዳን ይችላል የሚሉት ዶክተር ናትናኤል
ካንሰርን በትክክል መታከም እደሚገባ እና የካንሰር ታማሚዎች ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊ የህክምና ክትትል ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በህብረተሱ ዘንድ ያለው የካንሰር ህመም አይድንም የሚባለው የተሳሳተ አመለካከት ሊተካከል ይገባል ብለዋል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video
Source: Link to the Post