ጥቅምት 30 ቀን እንዲጀመር የተወሰነለት የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

ጥቅምት 30 ቀን እንዲጀመር የተወሰነለት የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲጀመር የተወሰነለት የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የክለሳ ትምህርት እንዲቀጥል መወሰኑንም አስተዳደሩ ገልጿል፡፡

አስተዳደሩ ተማሪዎችን ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጭ በተቀሩት ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የተቀመጡ ደረጃዎችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስከሚጠናቀቁ ድረስ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው የገጽ ለገጽ ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቢሮው ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post ጥቅምት 30 ቀን እንዲጀመር የተወሰነለት የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply