#ጥንቃቄትላንት እሁድ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደጋም ወረዳ “ወርቢ” በምትባል ቦታ በደረሰ እጅግ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።በአደ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/rZZfqN4SaJL6IiDsxopNV6KQkPI7B6I6KWCAvuD1X3EG8bbrgJY8emhHNwqmQZKAOUO9S85F-wv9lPnpevw1ucRkZRP2LwRzN4cIvlUQlDt5u6jXVDFzhq8LSR6lx24PF2lgBzjTiSgOmwmzDy1BINnbf2pP3bIU8aGO2uutTX_n4SIDGQHbnoMaoKLYRAIsbz9sCW9W7WfHrTxdAd4r6u86EKJt-7aSNoIcb4T28n5g2frY3c5dKmrMrsWJ-Y45tqKtBeXc2q-L6y7ocG4atrJHvkPKY8xixRC629lMhPVGa7qgUmhxuhS3uW4t4sDZbf4ZYthsAJvRJmKEiEx_4A.jpg

#ጥንቃቄ

ትላንት እሁድ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደጋም ወረዳ “ወርቢ” በምትባል ቦታ በደረሰ እጅግ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት 13ቱ ሰዎች መካከል መምህርት አስመሬ ጎሶማ እና አራት ልጆቿ ይገኙበታል። መምህርቷ የ18፣ 15፣ 8 እና የ1 ዓመት ልጆቻቸውን ይዘው ከአዲስ አበባ ወደ ጎሃ ጽዮን ቤተሰብ ጥየቃ እየጓዙ የነበረ ሲሆን፣ በአደጋው የእናት እና #የሁሉም_ልጆቻቸው ሕይወት አልፏል።

ለዚህ የትራፊክ አደጋ ምክንያቱ ቁልቁለት ቦታ ላይ ከባድ የጭነት መኪና በሕዝብ ማመላለሽ ሚኒባስ ላይ ስለወጣበት መሆኑን በደገም ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አሳውቋል።

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube

https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply