©ጥንቃቄ በወረባቦ ወረዳ አሸባሪው ትህነግ ጥሎት የሄደውን ቦንብ ሲነካኩ የነበሩ ሕጻናት ህይወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡ አሻራ ሚዲያ … መስከረም 05/2014 ዓ.ም ባህርዳር _ ኢትዮጵያ…

©ጥንቃቄ በወረባቦ ወረዳ አሸባሪው ትህነግ ጥሎት የሄደውን ቦንብ ሲነካኩ የነበሩ ሕጻናት ህይወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡ አሻራ ሚዲያ … መስከረም 05/2014 ዓ.ም ባህርዳር _ ኢትዮጵያ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ 018 ቁኖ ቀበሌ ወረራ በፈጸመበት ወቅት ንጹሐንን በግፍ መገደላቸውን ተገለፀ፡፡ በአሸባሪው ቡድን ላይ መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖና የአካባቢው ኅብረተሰብ በወሰዱበት ጠንካራ እርምጃ ሲደመሰስ የተረፈው ደግሞ አካባቢውን ጥሎ ቢፈረጥጥም መስከረም 03 /2014 አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በደረሰበት ከባድ ምት ጥሎት የሸሸውን ቦንብ ሲነካኩ የነበሩ ሦስት ሴት ሕጻናት ቦንቡ በመፈንዳቱ ህይወታቸው ማለፉን የወረባቦ ወረዳ የሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ጽሕፈት ቤት ገልጿል፡፡ ህይወታቸው ካለፉት ሕጻናት በተጨማሪ አንድ ታዳጊ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እየተደረገለት መሆኑም አሳውቀዋል፡፡ የወረባቦ ወረዳ የሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መሐመድ ሰይድ የጥፋት ቡድኑ ሽንፈት ሲደርስበት በየቦታው የሚጥላቸው የጦር መሳሪያዎች ስለሚኖሩ ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታልም ብለዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 Telegram :- https://t.me/asharamedia24 Yotube:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply