ጥገኝነት ተያቂ የሩስያ ጋዜጠኞች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መጨመሩ ተሰምቷል፡፡በሃገራቸው ካለው የሚዲያ ነጻነት ጋር በተያያዘ በሌሎች ሀገራት ጥገኝነት ጠያቂ ጋዜጠኖች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/YtCGRT2yT6HxwS9VjWEofGPOmz6QRF9Jk0PbX0bznBXnGMDJWDelEnRLSkSTpX_P4klNbdcfnouw76wwvVD94TtLyHoPDSyEV0Nh1ReqZ8bvp_jgZG24Q4tbnq27VFSju5AhT88LfMbkrxgAcHFpCuBa22CMIQsIOYBu6QzzB8uBNCDMMFvLzGhQFKIiRaiKHJdZohXn80MePSDLrPzty_Q0l_BiNLFI0N3MbrS31VwECGSVxaIm3NwVF1EyGMmAZBxqCJ0psxX3nrap12ZLDJf5s2QnQYf0wBBwynS60WI086kLhFWmcTnhH97Wwgb3ZX0fwBnTwGSkeYKylF3rcw.jpg

ጥገኝነት ተያቂ የሩስያ ጋዜጠኞች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መጨመሩ ተሰምቷል፡፡

በሃገራቸው ካለው የሚዲያ ነጻነት ጋር በተያያዘ በሌሎች ሀገራት ጥገኝነት ጠያቂ ጋዜጠኖች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተገልጻል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ 1ሺህ 800 ያህል ጋዜጠኞች ሀገራቸውን ጥለው በመውጣት በተለያዩ ሀገራት በጥገኝነት እየኖሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የሩስያ ዜግነት ያላቸው ጋዜጠኞች ሃገራቸው ጥለው ለመውጣታቸው ዋነኛ ምክንያት ጋዜጠኞቹ ሀገራቸው ከዩክሬን በገጠመች ጦርነት ምክንያት እየሰሩት ካለው ዘገባ ጋር በተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

ባሁኑ ሰአት በሃገሪቱ ከ300 በላይ ጋዜጠኞች እስር ላይ እንደሚገኙ ያስታወቀው ዘገባው ባለፉት ሁለት አመታት ከ20 በላይ ጋዜጠኞች በሰሯቸው ዘገባዎች ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል ብሏል፡፡

ሩስያ በአለም የሚዲያ ነጻነት እና የጋዜጠኞች መብት ጥሰት በጉልህ እያንጸባረቀች ትገኛለች ያለው አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ሲፒጄ በሃገሪቱ ሚዲያ እየሞተ ይገኛል ሲል ገልጻል፡፡

የአለም ሃገራት የሚዲያ ነጻነት የሚገመግመው ፕረስ ፍሪደም ኢንዴክስ ሩስያ 180 ሃገራት 164ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply