ጥፋታችንን ሳናውቅ ነው የባንክ አካውንታችን የተዘጋው ሲል ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ገለጸ። ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የድርጅቱ የሂሳብ አካውንት እና የስራ አስፈጻሚው አካውንት መዘጋቱን በዛሬው…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/fobmadU03zqBx2wJl4_IaZ6oaf03jmq94lGwuXDn6Swjl9GxadyANUwfYhK9t2ijWDxONegFjuoE_sPgD3V8SN-sK2iFz5715XFu0JgV1y6EJCkyw6b-Pn2JMfWCoLpTC9mbrFc4jzCLtpp_MNSm4iryvKM65giEyC1sQWNrjZoB7fBnk-kb3dMuOE1sawI88_fEZdlHS5-EbkEr6QpTwciradeyK3Nc3LP01qwpdmAc9QSaQbzL3ekkZ5imscgZFmjJmxkJQatDdeBptugKyuRRe3ffxlOxEmeNwblXhAH8vaGkg7Y1wtHECL0Mh3IF0qPJbkOeQyUHonDTWFVFTA.jpg

ጥፋታችንን ሳናውቅ ነው የባንክ አካውንታችን የተዘጋው ሲል ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የድርጅቱ የሂሳብ አካውንት እና የስራ አስፈጻሚው አካውንት መዘጋቱን በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የድርጅቱ ሶስት አካውንቶች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውን የገለጸው ፐርፐዝ ብላክ፣ የሚደርሰውን ኪሳራ እርምጃውን የወሰደው አካል ይወስዳል ብሏል።
ምንም አይነት ወንጀል ሰርተን አይደለም አካውንታችን የተዘጋው ያለው ድርጅቱ፣ ጥፋት ሰርተን ከሆነም በግልጽ ይነገረን ብሏል።

የባንክ አካውንታችን ያለ በቂ ምክንያት ከተዘጋ 72 ሰዓታት አልፎታል፣የሀገሪቱ ህግ የሚከበርበት ሁኔታ መረጋገጥ አለበት ሲልም ነው የገለጸው።

መንግስት ህግ የማክበርና የማስፈጸም ሀላፊነት አለበት ያሉት የፐርፐዝ ብላክ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሀ እሸቱ፣ እኛም ለህግ ተገዢ የማንሆንበት መንገድ የለም፣ነገር ግን ስርአቱን በጠበቀ መንገድ መሆን ይገባል ነው ያሉት።

ከየትኛውም አካል የደረሰው ምንም አይነት ደብዳቤ አለመኖሩን የገለጸው ፐርፐዝ ብላክ፣ ለከፍተኛ ችግር መጋለጡን አስታውቋል።
ይህ በመሆኑም ተቋሙ የሰራተኞች ደሞዝ ጨምሮ የፕሮጀክቶቹን ስራ ማስኬድ እንዳልቻለም ገልጿል።
የተሽከርካሪ ነዳጅ እንኳን መግዛት የማይችልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰም ነው ያስታወቀው።
ስራ ከጀመረ ሶስት አመታትን ያስቆጠረው ድርጅቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡን አስታውቋል።

ባለፉት ሶስት አመታት ተቋሙ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል
የተቋሙ መነሻ ካፒታል ከ1 ቢሊዮን ብር ወደ 2.4ቢሊዮን ብር ካፒታል መድረሱን አስታውቋል።
አሁን ላይ ድርጅቱ 1 ሺህ 300 የሚጠጉ ቋሚሰራተኞች ሰራተኞች እንዳሉትም ጨምሮ ገልጧል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply