ጦርነቱ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የጣለን ፅንፈኛ ቡድን አድኖ የመያዝ ግብ ያለው ነው – ዶክተር ቀንአ ያደታ

ጦርነቱ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የጣለን ፅንፈኛ ቡድን አድኖ የመያዝ ግብ ያለው ነው – ዶክተር ቀንአ ያደታ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጦርነቱ ተራ ወንጀለኛን የማፈላለግ ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የጣለን ፅንፈኛ ቡድን አድኖ የመያዝ ግብ ያለው መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀንአ ያደታ ተናገሩ።

ፅንፈኛው ቡድን እያሰራጫቸው ያሉ አሉባልታና የሀሰት መረጃዎችን አስመልክቶ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሃሰት መረጃዎቹን ማሰራጨት የጀመረው ቡድን የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ÷ ከውጭ ሀገር ጋር ሆኖ የትግራይን ህዝብ እየወጋ ነው የሚል የማይጨበጥ ወሬ ያሳረጫል ብለዋል።

ይሄው ቡድን ሰራዊቱ በታላቅ ጥንቃቄና ሙያዊነት ቡድኑን ነጥሎ ለማጥቃት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ሰአት ንፁሃንን እና መሰረት ልማት ላይ ጥቃት ይፈፅማል የሚል ማደናገሪያንም እየነዛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሄው ቡድን ህግ የማስከበር ስራውን የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ ማቅረቡን ያነሱት ሚኒስትሩ ይህም ስህተት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም በመግለጫቸው የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ የማንንም የውጭ ኃይል ድጋፍ ሳይፈልግ የጥፋት ቡድኑን የመደምሰስ ቁመና እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም ሰራዊቱ የትኛውንም ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ ድጋፍ አያስፈልገውም ቡድኑን ለማጥቃት የውጭ ድጋፍ አልጠየቀም አይጠይቅምም ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ መከላከያ ሰራዊቱ የሚወስደውን ህግን የማስከበር እርምጃ በጥንቃቄ እያከናወነ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

የትግራይ ህዝብ የጥፋት ቡድኑን ሴራ በመገንዘብ ለጉዳት እንዳይዳረግም አሳስበዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት በዘራፊው የህወሓት ቡድን ላይ በርካታ ድል እየተቀዳጀ ይገኛልም ነው ያሉት በመግለጫቸው።

ሚኒስትሩ ህዝቡ እያሳየ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የትግራይ ልዩ ሀይልም አጥፊ ቡድኑን አሳልፎ በመስጠት ህዝብና ሀገርን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

 

The post ጦርነቱ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የጣለን ፅንፈኛ ቡድን አድኖ የመያዝ ግብ ያለው ነው – ዶክተር ቀንአ ያደታ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply