
ጥቅምት 2013 በትግራይ ክልል ተጀምሮ ወደ አጎራባች ክልሎች ተስፋፍቶ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ እነሆ አንድ ወር አልፎታል። ይህ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት በተጀመረው የሰላማዊ መንገድ የሚቋጭ ከሆነ ቀጣዩ ከባድ ሥራ በጦርነቱ ከፍተኛ ወድመት የደረሰባቸውን አካባቢዎች እና መሠረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት ይሆናል። ለዚህስ ምን ያስፈልጋል?
Source: Link to the Post