ጫኝና አውራጆች ኅብረተሰቡ ላይ ይፈጽሙት የነበረውን እንግልትና ችግር ለመፍታት አዲስ አደረጃጀት ተግባራዊ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።የቢሮው ኃላፊ…

ጫኝና አውራጆች ኅብረተሰቡ ላይ ይፈጽሙት የነበረውን እንግልትና ችግር ለመፍታት አዲስ አደረጃጀት ተግባራዊ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት፤ ጫኝና አውራጆች ለሕዝቡ ምሬት ምንጭ በመሆን በተለያዩ ሕገ-ወጥ ተግባራት በመፈፀም ዜጎችን ሲያውኩ በመቆየታቸው በአዲስ መልክ ማኅበራት እንዲደራጁ ተደርጓል።

በመዲናዋ የሚገኙ ጫኝና አውራጆ ከማኅበረሰቡ አቅም በላይ ክፍያ በመጠየቅና የኅብረተሰቡ የጸጥታ ስጋት በመሆን ምሬት መፍጠራቸውን ጠቁመው፤ ጫኝና አውራጆችን መልሶ የማደራጀት ሥራው ከአራት ወራት በፊት ለአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ጸጥታ ቢሮ ተሰጥቶት ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በአደረጃጀቱ መሠረት አራት ሺሕ 829 አባላትን የያዙ 399 ጫኝና አውራጅ ማኅበራት በአዲስ መልክ መቋቋማቸውን አስታውቀዋል።
ማኅበራቱ በአግባቡ ሥራቸውን እያከናወኑ ለጸጥታ ኃይሎች ስጋት ሳይሆን አጋዥ የሚሆኑበትን ኹኔታ መፈጠሩን አመላክተዋል።
ማኅበራቱ ሕግና መመሪያን ተከትለው እንዲሠሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ጸጥታ ቢሮ በኩል አዲስ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶላቸው በፍትህ ሚኒስቴር አማካኝነት መጽደቁንም አስታውቀዋል።

በደንቡ ላይም የጫኝና አውራጅ ማኅበራት ሥልጣንና ኃላፊነት የተገለጸ ሲሆን፤ ለእያንዳንዱ ለሚወርድና ለሚጫን ዕቃ ዓይነት ተመን ወጥቶለታል ሲሉ አስረድተዋል።
አዲስ በተዘጋጀው ደንቡ ዙሪያ ለጫኝና አውራጅ ማኅበራቱ አባላት በቂ ሥልጠናዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ማኅበራቱ ከዚህ ቀደም ስምሪት ይሰጣቸው የነበረው በሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ የሠላምና ጸጥታ ቢሮ ማኅበራቱን ከማደራጀት ጀምሮ አጠቃላይ አካሄዳቸውን በመገምገም ስምሪት የሚሰጥበት አሠራር መፈጠሩን የቢሮው ኃላፊዋ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ማኅበራቱ የሥራ ዕድል ፈጥረው አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በተቀመጠላቸው የዋጋ ተመን መሠረት እንዲሠሩ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአፈጻጸም ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች እንዳሉም ጠቁመው፤ ማኅበረሰቡን አጋዥ የሚሆን አደረጃጀት እንጂ በማኅበረሰቡ ላይ ምሬት ሊፈጥር የሚችል አደረጃጀት እንዳይኖር ቢሮው ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply