You are currently viewing “ጭምብሉን አውልቆ በግልጽ ይፋ የታወጀውን መንግስታዊ ጸረ አማራ ዘመቻን በተባበረ ሕዝባዊ ክንድ እንመክት!!!”       ጋሻ አማራ  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ህዳር 27 ቀን 2015…

“ጭምብሉን አውልቆ በግልጽ ይፋ የታወጀውን መንግስታዊ ጸረ አማራ ዘመቻን በተባበረ ሕዝባዊ ክንድ እንመክት!!!” ጋሻ አማራ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2015…

“ጭምብሉን አውልቆ በግልጽ ይፋ የታወጀውን መንግስታዊ ጸረ አማራ ዘመቻን በተባበረ ሕዝባዊ ክንድ እንመክት!!!” ጋሻ አማራ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የጋሻ አማራ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ:_ ጭምብሉን አውልቆ በግልጽ ይፋ የታወጀውን መንግስታዊ ጸረ አማራ ዘመቻን በተባበረ ሕዝባዊ ክንድ እንመክት!!! ከወርሃ ህዳር አጋማሽ ጀምሮ በወለጋ በሚኖሩ የነገደ አማራ ተወላጆች ላይ የተከፈተውን መጠነ ሰፊ መንግስታዊ የጭፍጨፋ ዘመቻን ጋሻ አማራ በቅርበትና በጥልቀት ተከታትሎታል። በእርግጥ ወለጋ የሰው ልጅ መታረጃ ቄራ ባደረገ ደረጃ በነገደ አማራ ተወላጆች ላይ አሰቃቂ ጭፍጭፋ መካሄድ ከጀመረ ከዓራት ዓመት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም የአሁኑን ከአስካሁን ከተደረጉት ጭፍጨፋዎች የተለየ ያደረገው አረመኔው የብልጽግና ቡድን ጭንብሉን አውልቆ ሙሉ በሙሉ ይፋ በሆነ ሁኔታ መንግስታዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ ከፍቶ በማጧጧፍ ላይ መሆኑ ብቻ የተለየ አድርጎታል። ጋሻ አማራ ይህንን ጭምብሉን ያወለቀውን የአረመኔውን የብልጽግና ጨፍጫፊ ቡድን ጸረ አማራ ዘመቻ ዛሬ ጭምብሉን ባወለቀበት ሁኔታ የተጀመረ አማራን የመጨፍጨፍ፣ የመዝረፍና የማፈናቀል ስራ ብቻ እየተገበረ ያለ ሳይሆን፤ በዚህ በአራት ዓመቱ ጭፍጨፋ ላይ ሙሉ በሙሉ እጁ ያለበት መሆኑን በማስረጃ በተደገፈ ያመነና ያወቀ መሆኑን ድርጅታችን ማሳወቅ ይወዳል። የብልጽግናው የኦሮሚያ ቅርንጫፍ በሆነው ኦህዴድ ግንባር ቀደም ዘመቻ መሪነት በልዩ ሃይሉ በተከፈተ የጭፍጨፋ ዘመቻ በምስራቅና በምእራብ ወለጋ ዞኖች አንገጉትንን ጨምሮ በበርካታ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋቸውን ማረጋገጥ ችለናል። ጋሻ አማራ ይህንን በነገደ አማራ ላይ የተከፈተውን መጠነ ሰፊ የጭፍጨፋ ዘመቻ አጅግ በጽኑ እያወገዘ በጭፍጨፋው ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ጭፍጭፋውን በማፈንና በዝምታ የተባበሩትን በሀገር ውስጥ ያሉትን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኮር ዲፕሎማቶችን የሞራል ተጠያቂነት ያለባቸው የከፍተኛ ወንጀል ታዛቢዎች መሆናቸውን በመገንዘብ ዝምታቸውን እናወግዛለን። በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የምትኖር ውድ የአማራ ሕዝብ ሆይ፡- በሽፍታ ጭምብል በሕዝባችን ላይ የተከፈተው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ዛሬ ጭምብሉን አውልቆ መንግስታዊ ጭፍጨፋ መሆኑን በይፋ ያሳወቀበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዝምታ እራሱን የቻለ ሚና እና ድርሻ ቢኖረውም ከሁሉም በላይ በዚህ አራት ዓመት ውስጥ በወለጋ፣ በመተከል፣ በምስራቅ ሸዋና መሰል ቀጠናዎች ውስጥ መጠነ ሰፊ የጭፍጨፋ እርምጃ ሲፈጸም እኛ እንደ ሕዝብ ማድረግ የሚገባንን ባለማድረግ በዝምታ በማለፋችን ዛሬ ለደረስንበት ይፋ መንግስታዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ ሰለባዎች ሆነናል። ጭፍጨፋው መንግስታዊ ዘመቻ ነው ማለት ምን ማለት ነው? የአንድን ሀገርና ሕዝብ ደህንነትና ህልውናን የመጠበቅ ቀዳሚ ሀላፊነት የሚገባው መንግስታዊ ኃይል የጭፍጨፋ ዘመቻን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው ምላሽ ዛሬ በወለጋ በኦሮሚያ ልዩ ኋይል ከበባ ስር ሆነው ማንም እንዳይደርስላቸው ተደርጎ እየተጨፈጨፉ ያሉትን ወገኖቻችን የኔ ነው የሚሉት መንግስታዊ ሥርአት እንደሌለ እና መንግስት ይድረስልን የሚለው ህዛባዊ ጩኸት ሰሚ የሌለው መሆኑን በተደጋጋሚ ቁልጭ አድርጎ ያሳየን እውነታ ነው። መንግስት ጨፍጫፊ በሚሆንበት ሕዝብ መካችና ተከላካይ ኋይል በመሆን የተደቀነበትን የህልውና አደጋ የማክሸፍ ሕጋዊ ሞራላዊና ብሎም ሰነ ተፈጥሮዓዊ መብትም ግዴታም የተሰጠው ነው። በአረመኔው የብልጽግና መንግስታዊ ቡድን የተከፈተውን ጸረ አማራ ዘመቻን እኛ የነገደ አማራ ተወላጆች ግዴታ አለብን ብለን እንደ አማራነታችን ጋሻ አማራ በጽኑ ያምናል። በዚህም መሰረት፦ 1ኛ – በሀገር ውስጥ ያለኸው መላው የአማራ ሕዝብ በክልልና በፌዴራል ላይ ያሉትን ጸረ አማራ መንግስት ተብዬውን አረመኔ የብልጽግናን ቡድንን ሙሉ በሙሉ ወደ ጎን አድርገህ ወገንህን እንድትታደግ ይሁን፤ 2ኛ – መላው የአማራ ታጣቂ ኃይሎች በሙሉ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ፋኖ፣ የአማራ ሚሊሺያና በመከላከያ ውስጥ ያለኸው የአማራ ተወላጅ በሙሉ በግልና በቡድን እየሆንክ በአስቸኳይ ወቅቱ የጣለብህን ታሪካዊ ኃላፊነት እንድትወጣ ጥሪ እናደርጋለን፤ 3ኛ – በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የምትኖረው አማራ ሁሉ በወለጋ እየተጨፈጨፉ ላሉ ወገኖቻችን አፋጣኝ የመድሀኒትና መሰል አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማድረስ ይቻል ዘንድ ድጋፍ እንድታደርግ ጥሪ እናቀርባለን። 4ኛ- በዳያስፖራ የምትኖር መላው የአማራ ተወላጅ በሙሉ ነገዳዊ ግዴታህን በገንዘንብ፣ በመረጃ፣ በዲፕሎማሲና በሌሎች ቁሳዊ ድጋፎች ወገኖቻችንን በመደገፍ አማራው ወገናችን ዘላቂ መፍትሄ እስኪያገኝ በጽናት በደጀንነት እንድትቆም ጥሪ እናቀርባለን። መንግስታዊን ዘመቻ በሕዝባዊ ዘመቻ እንመክት!!! በተባበረ የአማራ ክንድ የሕዝባችንን ህልውና እናስጠብቅ!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply