ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ ሰጪ ረቂቅ ፖሊሲ ሊፀደቅ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ረ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Xd4zI1jpiQlm3DSi_ug-DgMdr-MhjzBM4gvFEJz5yenmeAQ2ebhtMlSrVCEnzw1xh70zKO2vG2SjjAS6YCc1naS3aiNARCmjFAXjYag25Qnp5uYnWXgU4DPfKH3tLz-pkDYot8aIMriWpOxFUktc32y-JXzUDHH7d1L1niIp0DRwZePJGP_g_XMsiwI8PSq7e4V9TqPxrWRY5VocnMDfoQjoWSiKUid18Yd7nKZVcBW0WHJLW3AY8LqitUeOP5ybXI3JaXt3D0Ee3gh-Sxo-CxMjRdV6bRLSDxjv1N51kVEUtls9jUuw8jH31PMB0lVfwV4tRPBJI3hJqhY_RnIRQw.jpg

ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ ሰጪ ረቂቅ ፖሊሲ ሊፀደቅ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ረቂቅ ፖሊሲ በአስቸኳይ ጸድቆ ወደ ስራ እንዲገባ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት እንዲህ ዓይነት ፖሊሲዎች ቢያስፈልጓትም ሳይኖሯት ቆይቷል ሲሉ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር የፕሮግራም ዳይሬክተር ቤተልሔም ደጉ ተናግረዋል፡፡
ፖሊሲው በሴቶች ላይ የሚደርስን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከልና ከለላ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ፖሊሲውን ለማርቀቅ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀላፊነቱን ወስዶ የሰራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያዎች ሴቶች ማህበርም የቴክኒክ ኮሚቴ አባል በመሆን በሂደቱ በዋናነት መሳተፉ ታውቋል፡፡

ይህ ፖሊሲ ከሌሎች የሴቶች መብት ላይ ካተኮሩ ህግና መመሪያዎች የሚለይዉ ቀደም ሲል ትኩረት ያልተሰጣቸዉና እንደቀላል የሚታዩ ከቃል ጀምሮ ያሉ የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በአቤል ደጀኔ

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply