ፀሐይ ባንክ በዛሬዉ እለት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡ባንኩ በ30 ቅርንጫፎቹ ዛሬ ወደ ስራ መግባቱን ነዉ ያስታወቀዉ፡፡ባንኩ በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የተፈረመና በ734 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/ZtAtWNf2G49HpXAeCfxiXZ0nhtF5Ov8XggPOYRfSh6PyNEGCOOuS-ud1dRIgSo3XvQbwNdayKA3hGy9mFSZ0rD_Xhnm6shfsZ-5uefVVnn0RoUYpy7SgHTO5bzVkPqkGb24tl7rWXdreqivjGtyj61SogHNBwVWFVnJGWVdWh9k9GDKNeFVIZawmIFR0wuRwkuZTnzRj5uXAX1HHYDHvmszm1mmQ16taQCnwgEkTlLvsvnu1ibbnzzdoELpz84OfiuefGVaZjOlgo9Upj9A05PcIX1aH0CccAhHSXEWuPAFI14AQ4ZusbI8BldDaUbSeEV77sftbEIXRmud0kq2fEw.jpg

ፀሐይ ባንክ በዛሬዉ እለት በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

ባንኩ በ30 ቅርንጫፎቹ ዛሬ ወደ ስራ መግባቱን ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

ባንኩ በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የተፈረመና በ734 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ተቋቁሟል፡፡
“ለሁሉ” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 2014 በይፋ ሥራ የጀመረዉ ባንኩ፣ ዝቅተኛ የአክሲዮን ግዢውን ከብር 100 ሺህ በመጀመር፣ በ373 ባለአክሲዮኖች መመስረቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

“ለሁሉም የሆነ ባንክ” እንዲሆን የአገልጋይነትን ዕሴትን ተላብሶ ስራ ጀምሯል የተባለው ባንኩ፣ ዛሬ 30 ቅርንጫፎች የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡
በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ፣30 ባንክ እና 40 የማይክኦሮ በአጠቃላይ ከ80 በላይ የፋይናንስ ተቋማት እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
የባንኮች ተልእኮ የህዝብን የቁጠባ ባህል ለማዳበር እና የብድር አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ መሆኑን ጠቁመዉ፣ በአሁኑ ወቅት ለባንኮች በገበያ ደረጃ የሚያሳስብ ነገር እንደሌለም አመልክተዋል፡፡

ዘግይተው ገበያውን የተቀላቀሉ ባንኮች በቀላሉ ስኬታማ መሆን የሚችሉበት የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት ዋና ገዥዉ፣
ገበያው ለውጭ ባንኮች የሚከፈት መሆኑ አይቀሬ በመሆኑ ለሚገጥማቸዉ ዉድድር ራሳቸዉን አዘጋጅተዉ እንዲጠብቁም አሳስበዋል፡፡
ጸሃይ ባንክ በይፋ ስራ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ለ4 ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ማለትም፤
ለጌርጌሴኖን 300ሺህ ብር፣ለኒያ ፋውንዴሽን 300ሺህ ብር፣ለኩላሊት ህመምተኞች በጎአድራጎት ድርጅት 500ሺህ ብር እንዲሁም ለኢትዮጲያ የልብ ህሙማን ማእከል 500ሺህ ብር የስጦታ ገንዘብ አበርክቷል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply