ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል በሆነው በህወሀት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ወታደራዊ አሰላልፍን ለጠላት ይፋ ከማድረግ መቆጠብ እንደሚያስፈልግ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ…

ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል በሆነው በህወሀት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ወታደራዊ አሰላልፍን ለጠላት ይፋ ከማድረግ መቆጠብ እንደሚያስፈልግ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ…

ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል በሆነው በህወሀት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ወታደራዊ አሰላልፍን ለጠላት ይፋ ከማድረግ መቆጠብ እንደሚያስፈልግ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ህወሀት አሁን ላይ የተስፋ ቆራጭ የሆነ አገርን የማፍረስና የመጨረሻውን የአጥፍቶ ጠፊ እርምጃን በመከላከያ ሰራዊት ላይ መውሰዱ ነውር ተብሎ የሚወገዝ የክህደት ተግባር መሆኑን ነው መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ የገለፀው። ይህ በህወሀት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ የአማራም ሆነ ሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በአፈና ላይ ካለው ከትግራይ ህዝብ ጎን በመሆንና ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን ሊያሳዩ ይገባል ሲልም አክሏል። የአማራ ህዝብና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ያለምንም መከፋፈል ነቅተው አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ያሳሰበው መቶ አለቃ ማስረሻ በትግራይ ክልል ያሉት የፀጥታ አካላትም በሽብር ተግባር ለተሰማራው ለህወሀት ስልጣን ሲባል ያልተገባ መስዋዕትነት መክፈል የለባቸውም ሲልም አክሏል። በመሆኑም በትግራይ ያለው የፀጥታ ሀይል አባላት ከህወሀት እጅ እና አፈና ሸሽተው ወደ አማራ ክልል ቢገቡና እጅ ቢሰጡ ህዝቡ በተለመደ የእንግዳ አቀባበል ባህሉ ተቀብሎ እንደሚያድናቸው አስታውቋል። የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴው እንዲሰክን የገለፀው መቶ አለቃ ማስረሻ አክቲቪስትና የሚዲያ ባለሙያዎች የአማራን ህዝብ በጠላትነት ለፈረጀው ቡድን የፀጥታ ሀይል አሰላለፍንና ስምሪትን አሳልፎ ማውጣት ተገቢ አለመሆኑን አውቀው እንዲቆጠቡ አሳስቧል። በጥቅም የሚገዟቸውን የራሳቸውን መዋቅር ተጠቅመው ጉዳት እንዳያደርሱም ህዝቡ ለሰላም ዘብ በመቆም ከፀጥታ አካሉ ጋር መናበብ አለበት የሚል መልዕክቱን አስተላልፏል። የአማራ ህዝብ በዋናነት የተመልካችነትና ራስን፣አካባቢን፣ህዝብንና ሀገርን ነቅቶ መጠበቅ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብሏል። በአማራ ላይ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ላሉ ጥቃቶችም ለጠፋው የአማራ ህዝብ ደም መንግስትን ጨምሮ እጃቸው ያለበትን አካላት በአለም አቀፍ ፍ/ቤት የምንጠይቅበት ጊዜ ይኖራል፤ የጊዜ ጉዳይ ነውም ብሏል። ከመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻችን የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply