ፀረ ዐማራው ዘመቻ ባስቸኳይ ይቁም!!!! ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአማራ ሚድያ ማእከል… ሚያዚያ 11 2013 አ/ም ብሩህ ነበልባላዊ ላንቃ! የ…

ፀረ ዐማራው ዘመቻ ባስቸኳይ ይቁም!!!! ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአማራ ሚድያ ማእከል… ሚያዚያ 11 2013 አ/ም ብሩህ ነበልባላዊ ላንቃ! የሚያበራ … ፍጹም ደማቅ … የሚያሞቅ ጃኖ፤ ነፍስን የሚታደግ የሰማያት ፍጹም ሽልማት፤ ቅመመ ብዙ – ልዩ ጣዕም፤ ሁሌ እንደ አሸተ የሚኖር ያመረበት። እርጅና ከቶም ዝር የማይልበት – ሀመልማለ ህብሬ፤ የውስጠት – ለእኛ ሰላማዊ ዕንቁ – ነው አማራነት፡፡ ለፀረ አማራ ሃይሎቹ ግን አንጡራ ጠላት፤ ለባላንጣው የፋመ ረመጥ። የእኛ የርትዕ – ክብረ – ዝናር፤ የእኛነታችን ልዕለ – ባለአደራ፤ የጥቁር ደም የግንባር ማህተም፤ብርቅዬ ነው አማራነት። ወርደ ሰፊ ማንነት፤ ደንበር ዬለሽ ሐርግ ነው አማራነት፡፡ በተጋድሎ ድል አብዝቶ የተቀለበ! የአሸናፊነት በትረ – ሰገነት! የነፃነት – ቅዱስ መንፈስ። ፈርጥ ነው አማራነት፡፡ የዚህ ማንነት ባለቤት ዐማራው ላለፉት 30 ዓመታት ተዋራጅና ተሸማቃቂ ተደርጓል፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅሞቹ ተነጥቀዋል ከምስራቅ፣ ከደቡብ፥ ከምእራብ፣ ከመሀል ኢትዮጵያ መኖር አትችልም ተብሎ ሀብት ንብረቱ ተነጥቆ ሲባረር ኖሯል። ትናንት በወተር፥ በአሰቦት፥ በእንቁፍቱ ገደል ተወርውሯል። ትናንት በአሶሳ፥ በጉራፈርዳ፥ በቡራዩ፥ በለገጣፎ ተገድሏል፥ ተፈናቅሏል። ዛሬ ግን ከዬት ወዴት ይሰደድ? ከመተከል፥ ከሰሜን ሸዋ፥ ከጎንደርስ ወዴት መሰደድ ይቻላል? አዎ ፀረ ዐማራው ሃይል ባለ በሌለ አቅሙ በዐማራው ላይ ዘምቶ እያጠቃን ነው። ይህ ወረራ ባስቸኳይ መገታት አለበት። ይህ የግፍና የጥጋብ ወረራ እንዲገታ ለዐማራው ህልውና ሌት ከቀን የሚሰራው አዴኃን ፀረ ዐማራው ዘመቻ ዛሬውኑ እንዲቆም በጥብቅ ያስጠነቅቃል። ዐማራው ከዚህ በኋላ ይህንን የመሰለውን ጥቃት የሚሸከምበት ትከሻ ከቶውንም አይኖረውም። ጠላትም ሆነ ወዳጅ ይህንን ጠንቅቆ ይረዳው። አዴኃንም ሆነ የቆመለት የዐማራ ህዝብ ዛሬ እየደረሰበትን ያለውን መፈናቀል፣ መገፋት መገለልና የዘር ማጽዳት እርምጃ ታግሶ የዘለቀው የሁሉም የሆነ ሃገርን ቀጣይ በማድረግ እንጂ የብረትን ላንቃ ሳቢ ክንድ ያነሰው በመሆኑ አይደለም። ስለዚህም በዐማራው ላይ የተነጣጠረው ጥቃት ዛሬውኑ እንዲቆም አዴኃን ፀረ አማራውን ሃይል በጥብቅ ያስጠነቅቃል። መንግስትም ዛሬ ነገ ሳይል ቁጥር አንድ ሃላፊነት የሆነበትን የዜጎችን መብት ባለው አቅሙ ሁሉ እንዲያስከብር በጥብቅ እናሳስባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዐማራው ራሱን ለመከላከል በሚፈጠር ውድመት ዐማራው ተጠያቂ እንደማይሆን በዚህ መግለጫ አበክረን እናስጠነቅቃለን። ጥሪያችን ወገናችንን ፈጥኖ መታደግና የዐማራው ህልውና ተጠብቆ ዐማራው በመላው ሀገሪቱ የመስራትና የመኖር መብቱ እንዲከበር ነው። በመሆኑም የጥቃቱ ሰለባ የሆንከው ወገናችን ዐማራ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ ቁጭት እና እልክ ፈጥረህ በወገኖችህ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ልትቋቋም ግድህ ነው። ከሁሉም በላይ በጠላት ተከብበው፣ የሚልሱት እና የሚቀምሱት አጥተው፣ ሞትን ከቅርብ ርቀት በመጠባበቅ ላይ ላሉት ወገኖቻችን ከነፍስ አድን እስከ ነፃነት ድረስ ለሚሹት ጉዳይ ሳናመነታ በድምፃችን፣ በገንዘባችን እና በእውቀታችን እንድንደርስላቸው አዴሃን በተጠቂ ወገኖቻችን ስም ጥሪውን ያቀርባል። ዐማራው ከተከፈተበት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ራሱን ተከላክሎ ዘሩን ማትረፍ የሚችለው፣ ሲነቃ፣ ሲደራጅ እና ሲታጠቅ እንደሆነ አዴሃን አምኗል። ራሱን መከላከል ያልቻለ ማኅበረሰብ ተዋራጅ፣ ተገዥ፣ ተጨቋኝና በመጨረሻም ጠፊ እንደሚሆን ከታሪክ የታየና የታወቀ ነው። ስለሆነም በዐማራው ላይ እየሆነ ያለው መጠነ-ሠፊ ዘመቻ የሚያመላክተው ተራ ጥቃትና ጥላቻን ብቻ ሳይሆን፣ የነገዱን መጥፋት እንደመሆኑ፣ አዴሃን ሁለንተናዊ አቅሙን አጠናክሮ ዓላማውን ከሚጋሩት ኃይሎችና ቡድኖች ጋር በመተባበር ዐማራውን ከፈጽሞ ጥፋት የሚታደግበትን ማናቸውም ዓይነት ተገቢ ሥልት በመከተል የዐማራውን ኅልውናና ማንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በብቃት እንደሚወጣ ከምንጊዜውም በላቀ ቁርጠኝነት እንደሚንቀሳቀስና አባላቱም የተጠየቁትን ማናቸውም ዓይነት ተገቢ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን በፍፁም ቁርጠኝነት ያረጋግጣል። አዴሃን ባህርዳር ሚያዚያ 11 2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply