ፅንፈኛው ቡድን ደምስሼዋለሁ ብሎ የሀሰት ዜና ያሰራጨበት 21ኛ ክፍለጦር አሁንም በጀግንነት እና በከፍተኛ ድል  እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፅንፈኛው ቡድን ደምስሼዋለሁ ብሎ የሀሰት ዜና ያሰራጨበት 21ኛ ክፍለጦር አሁንም በጀግንነት በከፍተኛ ድል እየገሰገሰ መሆኑን የክፍል ጦሩየኦፕሬሽን ምክትል አዛዥ ኮሎኔል መንግስቱ ደሴ ተናግረዋል።

በራያ ግምባር ህግን የማስከበር ተልዕኮ የተሰጠው ክፍለጦሩ ከዚህ ቀደም ጁንታው ተዘጋጅቶ ምሽግ ገንብቶ የነበረበትን ወሳኝ ቦታዎች እያስለቀቀ የገጠመውን ሰራዊትም እየደመሰሰ እየተጓዘ ይገኛል፡፡

በራያ ግንባር የ 21ኛ ክፍለጦር የኦፕሬሽን ምክትል አዛዥ ኮሎኔል መንግስቱ ደሴ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ÷ ክፍለጦሩ ከሃዲው ቡድን በሰሜን እዝ ላይ በፈፀመው ጥቃት በከፍተኛ የልብ ስብራት ውስጥ ሆኖ ህገ ወጡን ቡድን በጋለ ወኔና ቁጭት እየደመሰሰው ይገኛል ብለዋል፡፡

ሀሰት የሁል ጊዜ ተግባሩ የሆነው የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ደምሽሼዋለሁ ያለው ክፍለጦር በየጦር አውዱ ድል እየተቀዳጀ ቡድኑን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ይገኛልም  ብለዋል፡፡

የ21ኛ ክፍለጦርን ከባድ ጥቃት መቋቋም ያቃተው የከሃዲው ቡድን ሰራዊትም በአብዛኛው እየተማረከ ጥቂቱም እየፈረጠጠ ድል  እየተነሳ ይገኛል ብለዋል፡፡

ክፍለጦሩ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያም  የጁንታውን ኮንክሪት ምሽግ ዶግ አመድ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡

የአየር መቃወሚያውንም ከጥቅም ውጪ ከማድረጉም ባለፈ ብረትለበስ ምሽጎችና የመሳርያ ማከማቻወቻቸውን ማጥቃት መቻሉን ገልጸዋል።

በሀይለሚካኤል ዴቢሳ

The post ፅንፈኛው ቡድን ደምስሼዋለሁ ብሎ የሀሰት ዜና ያሰራጨበት 21ኛ ክፍለጦር አሁንም በጀግንነት እና በከፍተኛ ድል  እንደቀጠለ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply