ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በሲዳማ ክልል እየተካሄደ ነው

ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በሲዳማ ክልል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሚሊኒየም አደባባይ ከለሊቱ 12 ሰዓት በጀመረው በዚህ የድጋፍ ሰልፍ ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተውጣጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ነዋሪዎቹ ከሀዲውን ቡድን በሚያያወገዙ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በሚደግፉ በተለያዩ መፈክሮች ታጅበው ነው በሰልፉ ላይ የተገኙት።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በፅንፈኛው ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር እርምጃ በሁሉም መንገድ እንደሚደግፉም የሰልፉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በህዝቦች መሰዋዕትነት የተገነባች በመሆኗ በእናት ጡት ነካሽ ጁንታዎች አትፈርስም ያሉት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም የሚጠበቅብንን ሁሉ ድጋፍ እናደርጋለንም ብለዋል።

The post ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በሲዳማ ክልል እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply