ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ። ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው ባለፈው ሐሙስ የካቲት 14 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሲሆን፤ «ረብሻ ለመቀስቀስ » ሞክረሃል መባሉንም ቀጣሪ…

ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው ባለፈው ሐሙስ የካቲት 14 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሲሆን፤ «ረብሻ ለመቀስቀስ » ሞክረሃል መባሉንም ቀጣሪው ድርጅት አስታውቋል።

አንቷን ጋሊንዶ የተባለው ጋዜጠኛ በቅርቡ የተካሄደውን የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤን አፍሪቃ ኢንተለጀንስ ለተሰኘ ልዩ ኅትመት ለመዘገብ ነበር ወደ አዲስ አበባ የተጓዘው።

ጋዜጠኛው ባለፈው ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን፣ 2016 ፍርድ ቤት መቅረቡን የገለጸው አፍሪካን ኢንተለጀንስ እስከ ፊታችን አርብ የካቲት 22 ቀን፣ 2016 ዓ/ም ድረስ እስሩ እንደተራዘመ ማረጋገጡን አስታውቋል።

ጋዜጠኛው «ያለምክንያት መታሰሩን » እንደሚቃወምም ገልጻል። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አንድ ማንነቱ እንዳይገለጥ የፈለገ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው ምንጭ ነገረኝ እንዳለው ከሆነ፦ ጋዜጠኛው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ሐሙስ ከሰአት የተያዘው ከአንድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባለስልጣን ጋር በተገናኘበት ወቅት ነበር።

አንድ የኦነግ አንድ ቃል አቀባይ ሐሙስ ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ የፓርቲያቸው አንድ አባል መታሰሩን ግን ከጋዜጠኛው ጋር በተገናኘ ይሁን አይሁን ማረጋገጥ እንደማይችሉም ለየፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

የአፍሪቃ ኢንተለጀንስ ኅትመት የምሥራቅ አፍሪቃ ክፍልን በኃላፊነት የሚመራው የ36 ዓመቱ ጋዜጠኛ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ2013 እስከ 2017 ኢትዮጵያ የኖረ እና «በኢትዮጵያ የመገናኛ አውታር ባለሥልጣናት»ም የሚታወቅ ነው ሲል የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አክሎ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ምላሽ አለመስጠታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply