ፈረንሳይ በጊኒ ኤምባሲዋን ዘጋች፡፡ፈረንሳይ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ጊኒ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲ ግንኙነት በማቋረጥ በሃገሪቱ የሚገኝውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን አስታውቃለች፡፡ውሳኔው የተሰ…

ፈረንሳይ በጊኒ ኤምባሲዋን ዘጋች፡፡

ፈረንሳይ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ጊኒ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲ ግንኙነት በማቋረጥ በሃገሪቱ የሚገኝውን ኤምባሲዋን መዝጋቷን አስታውቃለች፡፡

ውሳኔው የተሰጠው የፓሪስ ቁልፍ አጋር በሆነችው ኒጀር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የመጨረሻዎቹ የፈረንሣይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው ከወጡ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡

“በኒጀር የሚገኘው የፈረንሣይ ኤምባሲ ቀጣይ እርምጃዎችን እስኪስውቅ ድረስ ተዘግቷል” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ቢገልጽም፣ ልዑኩ ከፓሪስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ግን እንደሚቀጥል ገልጿል።

በአዲሶቹ ወታደራዊ መሪዎች የተባረሩትን የፈረንሣይ አምባሳደርን ጨምሮ፣ አብዛኞቹ የኤምባሲው ሠራተኞች ከተወሰነ ወራት በፊት ሀገሪቱን ለቀው መውጣታቸው በኤኤፍፒ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

ወታደራዊው መንግሥት እኤአ ሀምሌ 26 የተመረጡትን የሀገሪቱ መሪ መሀመድ ባዙምን ከስልጣን ያስወገደ ሲሆን፣ ከፈረንሳይ ጋር የነበረውን የመከላከያ ስምምነቶችን ሰርዟል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባዙም በኒያሚ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply