
“ፈርሷል የተባለው የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከእነ ሙሉ ዩኒፎርሙ እና ትጥቁ በአንገር ጉትን እና በጊዳ አያና ወረዳ መግባቱን አሳውቁልን” ሲሉ ነዋሪዎች ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ “ፈርሷል የተባለው የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከእነ ሙሉ ዩኒፎርሙ እና ትጥቁ በአንገር ጉትን እና በጊዳ አያና ወረዳ ሀምሌ 9/2015 በ8 መኪና ተጭኖ መግባቱን አሳውቁልን” ሲሉ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። ይህ የኦሮሞ ልዩ ኃይል በተደጋጋሚ በተፈጸሙ የዘር ፍጅት፣መፈናቀል እና መሳደድ የወንጀል ድርጊቶች መሳተፉን ለአሚማ ያስታወሱት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ከህዳር 9/2015 ጀምሮ ለወራት የቆዬውን:_ ሀ) በምስራቅ ወለጋ ዞን:_ የኪረሞ፣ የሀሮ አዲስ ዓለም፣ የአንገር ጉትንና አካባቢውን እንዲሁም፣ ለ) በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን:_ የጃርዴጋ ጃርቴ፣ የአሙሩ እና የአቢ ደንጎሮ እና አካባቢውን የተደራጀ አማራ ተኮር ጥቃትን ከአሸባሪ ኦነጋዊያን እና ከሪጴሎላ፣ ከጋቸና ሲርና እና ከሌሎች የሽመልስ አብዲሳ ተልዕኮ ፈጻሚ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በመሪነት መምራቱን አስተውሰዋል። ከምስራቅ ወለጋ ዞን እና ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች በሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎችን በማንነታቸው ብቻ እያፈነ ወደ ነቀምት ማጊሪያ እንዲወሰዱ እና ለስቃይ እንዲዳረጉ ማድፈጉ የሚረሳ አለመሆኑን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ አሁንም ፈርሷል እየተባለ ሲወራለት የነበረው ይህ ኃይል ወደ ወረዳችን ተመልሶ መምጣቱ ለዳግም ማንነት ጥቃት ላለመሆኑ እርግጠኛ አይደለንም ብለዋል። ከዞን በ8 መኪና ታጥቆ የመጣው የኦሮሞ ልዩ ኃይል 4ቱ በአንገር ጉትን ሌላው 4 ደግሞ በጊዳ አያና ወረዳ ተራግፏል ተብሏል። ስለምን እንደመጣም የተጭበረበረ እንጅ የጠራ መረጃ የሚሰጠን በማጣታችን በጣም ተችግረናል የሚሉት ምንጮች አሁንም ከፍተኛ የሆነ ስጋት ስላለን ድምጽ እንድትሆኑን ስንል ቀድመን ጥሪ አቅርበናል ብለዋል። ትጥቁን ፈቶ ተበተነ የተባለው ማዘናጊያ ስለመሆኑ የነበረንን ጠንካራ ግምት ማረጋገጫ ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት ነዋሪዎች በተለይ ሚዲያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከጎናችን ሁኑ ሲሉ ጠይቀዋል።
Source: Link to the Post