ፈተና ለማስተጓጎል ሙከራ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ፈተና የመሠረዝ እርምጃ እንደሚወሰድ ትምህርት ሚንስቴር ገለጸ፡፡ሚንስቴሩ የ2014 የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/ASp7JPQJoefOAtDii9gFR3y-TFUpu3ndXWmOQQhVTnvxRfzOtrn9unyItN-CbZyIK0_-tkPVh4TWGCro7VySHbVJhIUauoXsk9zFg2VWXUwJyqZ1gSCBP27VAFQ44adhZs4BLoCx_52NmLusSdS0voQuDkV9qNk8eA9Z6f9PTGbqpEjv7i3b-uBvKMjhFZ95IS84EVbklBuM_HcsJ4nUwb39QbBzVvaiROY5ZVCpC0okVT89dQ3L8QI29nALq9Zw7offXYH-1vFS-qo6CkfaLZGjjD9Mx41Tb8fFmgKMu_lSGm4tdXEeJ4fKm_ZcORSrTG7_3RmsJ6rxx8tj_oJxtg.jpg

ፈተና ለማስተጓጎል ሙከራ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ፈተና የመሠረዝ እርምጃ እንደሚወሰድ ትምህርት ሚንስቴር ገለጸ፡፡

ሚንስቴሩ የ2014 የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በስኬት ተጠናቋል ብሏል::

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የ 2014 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ በደረሰ የድልድይ መናድ ምክንያት የአንድ ተፈታኝ ተማሪ ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።በአደጋው ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

በደብረታቦር ዩንቨርሲቲ ፈተናውን ለማስተጓጎል የሞከሩ አካላት መኖራቸው በመግለጫው ተመላክቷል።

ፈተና ለማስተጓጎል ሙከራ ባደረጉ ተማሪዎች ላይም አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ፈተና የመሠረዝ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply