ፊታውራሪ አመዴ ለማ

የአርሶ አደር ልጅ ናቸው እንደሳቸው አገላለጽ የገበሬ ልጆች የሚያልፏቸውን ብዙ ውጣ ውረዶች አልፈዋል፡፡ በጣሊያን ዘመን እስከ 4ኛ ክፍል የመማር ዕድል አግኝተዋል፡፡

በኋላ ላይ የሕግ ትምህርታቸውን ተከታትለው በዲፕሎም ተመርቀዋል፡፡ ከዚያም የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው በመምራት ላይ እያሉ በ1948 ዓ.ም የፓርላማ አባል እንዲሆኑ በሕዝቡ ተጠቁመው በመወዳደር ያሸነፉ ሲሆን በዚያን ጊዜ ከ300 የማያንሱ ልዩ ልዩ መጽሐፍትን ማንበባቸውን ይናገራሉ፡፡

ላመኑበት ጉዳይ ብርቱ ተከራካሪ በመሆናቸውም በወሎ በተካሄደው ጠንካራ ውድድር ለፓርላማ አባልነት በማሸነፍ የደሴን ሕዝብ ከወከሉት ሁለት እጩዎች አንዱ ሆነው አዲስ አበባ መምጣታቸውን ታሪካቸው ያወሳል፡፡ ፊታውራሪ አመዴ ለማ ለዕለቱ የምናብ እንግዳችን እንዲሆኑ በእየሩሳሌም ብርሃኑ ተጋብዘዋል ዮሐንስ አሰፋ ያስተናግዳቸዋል፡፡

ቀን13/05/2013

አዘጋጅ፡ዮሐንስ አሰፋ

የምናብ እንግዳ

The post ፊታውራሪ አመዴ ለማ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply