ፊንላንድ በነገዉ ዕለት ኔቶን ልትቀላቀል ነዉ፡፡ፊንላንድ በነገዉ ዕለት ኔቶን ልትቀላቀል መሆኑን የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ አሳዉቀዋል፡፡በኔቶ ዋና መስሪያ ቤት የፊንላንድን ባንዲራ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/bmx7tFUjC8hy_wl53ecN3mA2FDZEF2m_Aof_xEGe-Vx3uEMqAyhmRFUdWxixqyMxXbzDTXH0C2qAC8F3Bbths2RRHLVX77Ka-5GDEEiEQ75Sf4t4i2RonIYenl4JKVQMDQe9ympRI5tYhCkz2oh8slvKHiFpe0cUMyM3uitc_P0BJMzwvcL5p3E0xJsFFzCByGucB53DuE7TOuoY4KT5nx_S960MuYTl4fDYIuiFjKma9_F_1XuZzzVBYh0BwrQI82jMU2WxixSex45WEBKZ2E2k_3kc34lj2MY8aAlf6ZKRTitwnIu5Zu5gc01JXAeQnak0Kx0Te4cDliJwWZ_knA.jpg

ፊንላንድ በነገዉ ዕለት ኔቶን ልትቀላቀል ነዉ፡፡

ፊንላንድ በነገዉ ዕለት ኔቶን ልትቀላቀል መሆኑን የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ አሳዉቀዋል፡፡

በኔቶ ዋና መስሪያ ቤት የፊንላንድን ባንዲራ ለመጀመሪያ ጊዜ እንሰቅላለን፤ይህም ለፊንላንድ ደህንነት መልካም ቀን ይሆናል፤በተጨማሪም ለኖርዲክ አገራት ደህንነት እና ለኔቶ በአጠቃላይ መልካም ይሆናል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

የሲዉዲንም ደህንነቷ የተረጋገጠ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል ሲል የዘገበዉ ሮይተርስ ነዉ፡፡

ከዚህ ቀደም ፊላንድ ኔቶን እቀላቀላለሁ የሚል መግለጫ መስጠቷን ተከትሎ የዩክሬን እጣ ፋንታ ሊደርሳት እንደሚችል ከሩሲያ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷት ነበር፡፡

ይህን ተከትሎም የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር የአውሮፓ ሃገራትና አሜሪካ የሚደርሱት ውድመት ከደረሰ በኋላ መሆኑ እንዳሳሰባቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡

አሁን ፊንላንድ ኔቶን መቀላቀሏ እውን ሆኖ ለነገ ቀን ተቆርጦለታል ተብሏል፡፡

በእስከዳር ግርማ
መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply