ፋሲል ከነማን ለመደገፍ የተዘጋጀው አምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ በጎንደር ከተማ ተካሄደ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ከተ…

ፋሲል ከነማን ለመደገፍ የተዘጋጀው አምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ በጎንደር ከተማ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ከተ…

ፋሲል ከነማን ለመደገፍ የተዘጋጀው አምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ በጎንደር ከተማ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል ለማክበር ከሀገር ውስጥ እና ከወጭ ሀገር የተገኙ እንግዶች፣ የከተማው ነዋሪዎች፣ የክለቡ ደጋፊዎች እና የሥራ ኃላፊዎች “ለፋሲል ከነማ እንሮጣለን በተግባር እንደግፋለን”በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው ዛሬ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም በተካሄደው የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ መላኩ ሲሳይ፣ አምሳያው መኮንን እና ንጉሥ መንግሥቴ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሩጫውን በአንደኝነት ያጠናቀቀው መላኩ ሲሳይ እንደገለጸው “የክልላችን አርማ የሆነው የፋሲል ክለብ ለመደገፍ ሩጫለሁ ፤ በክለቡ ስም በመሮጥ አንደኛ በመውጣቴ ደስ ብሎኛል ብሏል። ሌላው ተወዳዳሪ አምሳያው መኮንን የፋሲል ክለብ ኩራታችን በመሆኑ ሁሉም ክለቡን መደገፍ እንዳለበት ተናግረዋል። ክለቡን ለመደገፍም እንደተወዳደረ ገልጿል። የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ኃይለማርያም ፈረደ ለፋሲል ክለብ የገቢ ማሰባሰብን ዓላማ ያደረገው ሩጫ በተገቢ መልኩ መከናወኑን ተናግረዋል። ሩጫውን በዚህ ወቅት ማድረግ የተፈለገውም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር የጥምቀት በዓል ለማክበር የመጡ እንግዶች እንዲሳተፉ ለማስቻል ነው ብለዋል። ለውድድሩ ከተዘጋጀው የቲሸርት ሽያጭ እና ከስፖንሰር ክለቡን ማጠናከር የሚረዳ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል። በተለይም የክለቡ ደጋፊ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስታድየም ገብቶ ለመደገፍ በመቸገሩ በቂ ድጋፍ ሳይሰበሰብ መቆየቱን የተናገሩት አቶ ኃይለማርያም ዛሬ የተደረገው ሩጫ መነቃቃትን ፈጥሯል ብለዋል። በሩጫው አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ፣ አርቲስቶች እና ሌሎችም የክብር እንግዶች ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል። በተያያዘም ተሳታፊዎቹ “ትኩረት ለመተከል!” በሚል በመተከል እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ መንግስትን ጨምሮ የሰው ልጅ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በተመሳሳይ ጥምቀትን በጎንደር ለመታደም፣ ራሳቸውንና አካባቢያቸውን ለማስተዋወቅ ሲሉ የተለያዩ የባህልና የኪነ ጥበባት ቡድኖች ተገኝተዋል። በጎንደር ከተማ ተገኝተው አካባቢውን እያደመቁት ካሉ የባህል ቡድኖች መካከልም በቅርቡ ራሱን ችሎ የተደራጀው የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ሳንኪ የባህል ቡድንና በዘር አጥፊው ትሕነግ ለበርካታ አማራዊ ወግና ባህላቸውን እንዳያሳድጉ ተከልክለው የኖሩት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ጠለምት የባህል ቡድንና ነዋሪዎች ይገኙበታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply