ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ25 ዓመታት የአፋን ኦሮሞ የስርጭት ጊዜ ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ ነገ ያካሂዳል

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ25 ዓመታት የአፋን ኦሮሞ የስርጭት ጊዜ ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባለፉት 25 ዓመታት የአፋን ኦሮሞ የስርጭት ጊዜ ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ ሊያካሂድ ነው።
የምክክር መድረኩ በነገው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ቤስት ዌስተርን ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል።
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ25 ዓመታት ጉዞው የአፋን ኦሮሞ ስርጭቱ በቋንቋ፣ ባህል አና ስነ ጥበብ እድገት እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያበረከተው አስተዋጽኦ ላይ የሚያተኩር ጥናታዊ ጽሁፍ ይቀርባል።
ፋና በቀጣይ ጊዜያት በዘርፉ የተሻለ ስራዎችን ይዞ በመቅረብ እና የአድማጭ ተመልካቾችን ፍላጎት ለማርካት በሚወስዳቸው የማሻሻያ እርምጃዎች ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችም በጥናታዊ ጽሁፉ ቀርበው ምክክር ይደረግባቸዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ የሚዲያ፣ የኪነ ጥበብ እና የስነጥበብ ባለሙያዎች፣ ምሁራን እንዲሁም የማህበራት ተወካዮች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

The post ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በ25 ዓመታት የአፋን ኦሮሞ የስርጭት ጊዜ ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ ነገ ያካሂዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply