ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን በክልል ጣቢያዎች እያከበረ ነው

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን በክልል ጣቢያዎች እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን በክልል ጣቢያዎች በማክበር ላይ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬቱ ባለፉት 25 ዓመታት የሰጠውን የሚዲያ አግልግሎት፣ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች እና በቀጣይ ራዕይ ላይ በማተኮር በዓሉን ከደንበኞቹ ጋር እያከበረ ነው፡፡

በዓሉ በዛሬው ዕለት በጅማ፣ ሻሸመኔ፣ ሐረማያና በደሴ ሲከበር፤ ነገ በደብረ ብርሃን በተመሳሳይ ይከበራል፡፡

ፋና ከየት ወዴት የሚል ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፣ በቀጣይ ጥንካሬውን ከፍ በማድረግ፣ ክፍተቶቹን አርሞ በተሻለ የሚዲያ አግልግሎት ለማምጣት ከመድረኮቹ ግብዓት ይሰበሰባል ተብሏል፡፡

በዓሉ አድማጮቹን፣ ደንበኞቹን እና ሰራተኞቹንም የሚያመሰግንበት መድረክም ጭምር ነው፡፡

The post ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ ዓመቱን በክልል ጣቢያዎች እያከበረ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply