“ፋኖነት ወንጀል አይደለም!!፤ የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው።” የአማራ ፋኖ በባህርዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

“ፋኖነት ወንጀል አይደለም!!፤ የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው።” የአማራ ፋኖ በባህርዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመጀመሪያ በዛሬው ዕለት በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት የተገኛችሁ መላው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ፣የከተማችን ጀግና ወጣቶች እና የከተማችን ነዋሪዎች ለማይሰበሩት ጀግና የአማራ ፋኖዎች ላደረጋችሁትና ላሳያችሁት ፍፁም አጋርነት ፣አንድነት እና አማራዊ ወንድማማችነት እናመሠግናለን። የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች ፤ የአማራ ፋኖ በሸዋ አመራሮች እና አባላት በዛሬው ዕለት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀረቡ። በሃሰት የተወነጀሉት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር እና በሸዋ ወንድሞቻችንና እህታችን የፌደራል ፖሊስ ባቀረበው አንዱ የክስ መዝገብ ውስጥ ዘጠኝ ተከሳሾች ሲሆኑ ስማቸው የሚከተሉት ናቸው:_ 1ኛ. ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ 2ኛ.መንግስቱ አማረ፣ 3ኛ.ማንችሎት እሱባለው፣ 4ኛ.ኖላዊት ይልሃል፣ 5ኛ.ሀብታሙ ማንደፍሮ፣ 6ኛ.ያሬድ መንግስቱ፣ 7ኛ.ምትኩ ጠብቀው፣ 8ኛ.ያስችላል ጌጤ እና 9ኛ.ኃይለማሪያም ተባባል ናቸው። ከሳሽ የፌደራል ፓሊስም የተሰጠኝ ጊዜ በቂ አይደለም የአስራ አራት(14) ቀን የጊዜ ቀጠሮ ድጋሚ ይሰጠኝ ብሏል። አሁንም የሚቀሩ ስራዎች አሉ በማለት ያቀረባቸው በርካታ ቢሆንሞ በዋናነት ግን ተጨማሪ የምስክርነት ቃል መቀብል እና ግብረ አበሮችን ተከታትሎ መያዝ እና ወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ማስረጃዎች ማሰባሰብ እና ሌሎች የሚሉ ናቸው። የተጠርጣሪ ጠበቆችም ፖሊስ የጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ተገቢ አይደለም። ከዚህ በፊት የተሰጠው የአስራ አራት ቀን በቂ ነበር በማለት ተከራክረዋል። እንዲሁም ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ኢ -መደበኛ አደረጃጀት ብሎ ቢጠራቸውም በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አዝማችነት፣ ኦርኔል ሞልተው እና ከተማ አሰተዳደሩ የትራስፓርት መኪና አቅርቦ የከተማው ህዝብ በተገኘበት የአማራ ህዝብ በገጠመው የህልውና ጦርነት ራሳቸውን መስዕዋት ለማድረግ የዘመቱ ፣የቆሰሉ እና የደሙ ናቸው። ለህዝብ ጠበቃ ፤ ለመንግስትም ቢሆን ዘብ የሆኑ እንጂ ከተከሰሱበት ወንጀል ጋር ፈፅሞ የማይገኙ ህዝብ ሃላፊነት ሊጥልባቸው የሚችሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው በማለት የተጠርጣሪ ጠበቆች ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል። ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ከሰማ በኃላ የአስር(10) ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጧል። በመሆኑም መጪው የችሎት ሐምሌ 19/11/2014 ዓ.ም ይሆናል ። ፋኖነት ወንጀል አይደለም!! የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply