You are currently viewing ፋኖን ትደግፋለህ በሚል ዳግም የታፈነው ወጣት አማረ አቸነፍ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ሊወሰድ መሆኑ ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመለከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 4 ቀን 2014 ዓ….

ፋኖን ትደግፋለህ በሚል ዳግም የታፈነው ወጣት አማረ አቸነፍ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ሊወሰድ መሆኑ ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመለከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 4 ቀን 2014 ዓ….

ፋኖን ትደግፋለህ በሚል ዳግም የታፈነው ወጣት አማረ አቸነፍ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ሊወሰድ መሆኑ ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመለከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ አማራዊ አንድነት እንዲኖር በንቃት በማህበራዊ ሚዲያ በመጻፉ በበርካቶች የሚታወቀው ወጣት አማረ አቸነፍ “ህግ ማስከበር” በሚል በአማራ ላይ የተከፈተውን የአፈና ዘመቻን ተከትሎ በግፍ ታስሮ መሰንበቱ ይታወቃል። ወጣት አማረ አሸነፍ በቆላድባ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረበት በ2,000 ዋስትና ከወጣ በኋላ በድጋሜ በማሰር ወደ ጎንደር 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል። ይሁን እንጅ ከሁለት ቀን ቆይታ በኋላ ወደ ማረሚያ ቤት ያስገቡት እንጅ አሁን ላይ ደግሞ ቤተሰቦቹ በቅርብ በማይገኙበት ልክ ዛሬም እንደ ትናንቱ አፍነው ወደ አዲስ አበባ ሊወሰዱት መሆኑ ተገልጧል። አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ትህትና በላይ፣ የአሻራ ሚዲያ እና የንስር ብሮድ ካስት ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲፈቱ በፍ/ቤት ቢታዘዝም ትዕዛዙ ተጥሶ ወደ አዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው እንዲመጡ መደረጉ ይታወሳል። ሻለቃ አንተነህ ድረስም የታች አርማጭሆ እና የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ተጥሶ በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ክስ እና ምስክር ከተገኘ በሚል እየተፈለገለት እንደሚገኝ ይታወቃል። በመጨረሻም ቤተሰቦቹ እና ጓዶቹ ሁሉም ለወጣት አማረ አሸነፍ ድምፅ እንዲሆነው ጠይቀዋል። ለዘገባው ንሥር ብሮድካስትን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply