“ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በመላው አማራ ክልል ተጀምሯል፤ የመከላከያ አዛዦች በየዞኑ ተልእኮ ተሰጥቷቸው ተሰማርተዋል።” ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 3…

“ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በመላው አማራ ክልል ተጀምሯል፤ የመከላከያ አዛዦች በየዞኑ ተልእኮ ተሰጥቷቸው ተሰማርተዋል።” ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ወሎ ዞን ያለውን ፋኖ ትጥቅ የማስፈታቱን ተልዕኮ እቅድ አዘጋጅቶ ደቡብ እዝ ጀምሯል። የእቅዱ መነሻ ነጥብ የአማራ ህዝብ ከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ይልቅ በኢ መደበኛ ለተደራጀው ፋኖ ይወግናል። ፋኖዎችም ይህንን ተማምነው ክንዳቸውን አፈርጥመዋል። የሚል ነው። ሌላው ሕወሓት የአማራ ክልልን ሲወር የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ከቀላል ጠመንጃ ጀምሮ ታንክና መድፍ ጥሎ መውጣቱ ይታወሳል። የአማራ ክልል መንግስት በዚያን ወቅት የህልውና ዘመቻ ጥሪ ለወጣቱ በማቅረብ ከሕወሓት የማረከውን የጦር መሳሪያ ለግሉ አድርጎጠ መታጠቅ እንደሚችል መመሪያ አውጥቶ ነበር። ወጣቱ ጥሪውን በመቀበል ጦርነቱ ውስጥ ገብቶ የነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ ታጥቋል። መከላከያ ዛሬ እኔ አልፈቀድኩም። ይህ መሳሪያ የእኔ ነው መልሱ በሚል መሳሪያውን በኋይል ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ነው። ፋኖም “እናንተ ጥላችሁት ሸሽታችሁ ከሕወሓት እጅ ከገባ በኋላ ከሕወሓት እጅ ነው የማረክነው” የሚል ነው። የአማራ ክልልም በዚያን ወቅት ያወጣውን መመሪያ እረስቶ ከመከላከያ ጋር ሆኖ ዘመቻውን እያስተባበረ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply