“ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ!” አሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እኛም ለምንሞትለት ህዝብ ሲ…

“ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ!” አሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ እኛም ለምንሞትለት ህዝብ ሲባል እኩይ ድርጊታችሁን እናስቆማለን። የክልሉ ህዝብ እና መንግስት የተለያዩ ናቸው። የክልሉን መንግስት የሚዘውሩት ስነ ልቦናቸው ተንበርካኪ እና የስልጣን ጥመኞች ናቸው። የተላላኪነት መንፈሳቸው፣ዕውቀት ጠልነታቸው ፣ አድርባይነታቸው እና አማራን አሳልፎ በመስጠት ፓለቲካውን ለማበላሸት በኦህደድ በኩል ውክልና የተሰጣቸው ናቸው። የአማራ ህዝብ ደግሞ በሃገረ መንግስት ያለውን ድርሻ ተነጥቆ የአምባገነኖች እና የአሸባሪ ሃይሎች መጫወቻ ከሆነ ሰነባብቷል። ስለሆነም የህዝባችን ጠላቶች ቀዳማይም ድሃራይም ቅጥረኛ ብአደኖች ናቸው። ስለሆነም ህዝባችንን እያስወረሩ በስልጣን መቀጠል ተገቢነት የሌለው አካሄድ በመሆኑ በሁሉም አቅጣጫ ያሰራችኋቸውን እውነተኛ የህዝብ ልጆች ፍቷቸው። ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ ። በሁሉም ዘርፍ እየተባላን የግፈኞችን ስልጣን የምናስቀጥልበት መሰረታዊ ምክንያት መቆም አለበት!! አማራነት /ሞት በማለት ሲልከስከስ የነበረው ሃይል ጭምርም በፋኖወቻችን ላይ ያደረገውን ክህደት አንረሳውም። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወድህ የሚታዩት መጓተቶች መሰረታዊ ምክንያታቸው የብልፅግና መዋቅር ቢሆንም በተለይ የአማራን የህልውና አደጋ በውል ያልተረዳው ቅጥረኛ ሃይል በጊዜ ከድርጊቱ እንድያቆም ብንወተውትም ሁኔታዎች ግን የባሳ መቀጠላቸው ዕረፍት ሊሰጠን አልቻለም። የአማራ ህዝብ የቅጥረኞች መናሃሪያ በመሆን እውነተኛ የህዝብ ታጋዮችን ጭምር ሲያስበላ መኖሩ ሳያንስ አሁንም ለህወሓታዊ ወረራ ምክንያት በመሆን ታጋዮቻችን አሳስሮ ተጨማሪ ጥቃት እንዲፈፀምብን አንሻም። ስለሆነም ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ባሉ አካባቢዎች የታሰሩ እና የተሳደዱ የፋኖ አመራር እና አባላቶች በይቅርታ ተፈትተው ለህልውናችን ተግዳሮት የሆነውን አሸባሪ ሃይልና ግብረ አበሮቹን በጋራ ልንታገል ይገባል። የአማራ ህዝብ በታሪክ ከስህተቱ እንዳይማር ያደረጋችሁ የፓርቲ ብር ተከፋዮች ሁሉ አሁንም ከፋኖ ላይ ያላችሁን የተዛባ አረዳድ በጊዜ ለማስተማር ያባከነውን ጊዜ ሁሉ እንድንፀፀትበት አታድርጉን። ጀግኖቹ የአማራ ልጆችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ!! ወንድሞቻችን የታሰሩት የግፈኞችን ስልጣን ለማስቀጠል በዱር በገደል አሸባሪን የታገሉ እንጅ የስልጣን ጥመኞች በሚፈብረኩት የብልፅግና አጀንዳ አይደለም። የአማራ ታጋዮችን በፖለቲካዊ መንገድ ማሰር የተለመደ ቢሆንም የአሁናዊ ዕስር ግን የሚለየው ህዝቡ በተለየ ሁኔታ የጥቃት ተጋላጭ እንድሆን መደረጉ ነው። ፋኖን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት የክልሉን ህዝብ እና መንግስት ተቀራርቦ የተቃጣበትን ጥቃት ለመመከት ወሳኝ ተግባር በመሆኑም ጭምር ነው። ፋኖን አታሳዱት!! የትርክት ሰለባ አታድርጉት!! በተያያዘም ጀግናውን የአማራ ልዩ ሃይል ከህዝቡ እና ከፋኖው ለመነጠል ሲያፈደፍድ የነበረው ሃይል ማን እንደነበርስ ታስታውሳላችሁ?? የማይበገረውንና ክንዱ የሚፋጀውን የቁርጥ ቀን የህዝብ ደጀን የሆነውን የአማራ ልዩ ሃይል ምንም ይሁን ምን ጀግንነቱን ጠላቶቻችን አሳምረው ያውቁታል። ለህዝቡና ለሚወዳት ሃገሩ የከፈለው መስዋአትነትን እኛ ወንድሞቹ እና የአማራ ህዝብ የሚረሳው አይደለም። አሁንም ከልዩ ሃይላችን ጎን በጋራ እንሰራለን። ታሪክም እንሰራለን። ነገር ግን የቅጥረኞችን አጀንዳ ተሸክሞ የድል ሺሚያ እያለ ስውር ድራማ የሚያስተናግደውን ሃይል ጭምር በኩራት እንፋለመዋለን። አሁን ሁሉም ነገር ገብቶናል። በጊዜ ሂደት የሚመጡትን መሰል ወረራዎች የምንቋቋምበትን መንገድ እኛ ም ሆነ ትውልዱ በሸላሉ የሚረሳው አይደለም። ጀግናውን የአማራ ልዩ ሃይል በትብብር እና በአስተማማኝ ሁኔታ እናግዘው!! እየከፈለ ያለው ውድ ህይወቱን ነው። ትርፍ እና ርካሺ ተወዳጅ ለመሆን ከህዝብ በተቃራኒ የቆማችሁ የልዩ ሃይል አመራሮች ጭምር አደብ ያዙ። ልዩ ሃይላችን በተረኝነት የሚናውዝን ከሃድ ጭምር በቁርጥ የሚታገል ይሆናል። የአማራን ህዝብ በኢኮኖሚ እና በህዝብ ቁጥር ጭምር ለማሳሳት የሚረገውን የሁለት አምባገነን ሃይሎች ጦርነቱ በደሙ ያከሺፋል። ለጥሬ ስልጣን ተብሎ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉም ሃይሎች እንድፋለሙትም እንጠይቃለን። በእኛ በአማራዎች ዘንድ ግን ትግላችን የምንኖርባትን ሃገር ፍለጋ ጭምር መሆኑ ይታወቅ። በሃገረ መንግስቱ የነበረን የዜግነት ድርሻ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በነፃነት ለመኖር እድልን የሚሰጥ አይደለም። ስለዚህ በህይዎት ለመኖር ደግሞ ወድ ህይወታችን ጭምር እያጣን የህዝባችንን ህልውና እናስቀጥላለን። ነገር ግን ከስርዓቱ ጋር የተጣላችሁ ወጣቶች እና ፋኖዎች ሁሉ ከጀግናው የአማራ ልዩ ሃይል ጋር በመተባበር ህልውናህን አስጠብቅ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply