You are currently viewing ፋኖ ማለት ምንድን ነው?”      ፋኖ አንተነህ ድረስ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …   ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ ወ/ሮ አዳነች አበቤ “ጽንፈኛ ፋኖ”…

ፋኖ ማለት ምንድን ነው?” ፋኖ አንተነህ ድረስ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ወ/ሮ አዳነች አበቤ “ጽንፈኛ ፋኖ”…

ፋኖ ማለት ምንድን ነው?” ፋኖ አንተነህ ድረስ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ወ/ሮ አዳነች አበቤ “ጽንፈኛ ፋኖ” ስትል የፋኖን ስም ለማጥፋት እና ከተነሳበት አላማ እና ግብር ውጭ ጠባጫሪ እና የወለጋን አጀንዳ ለማስቀየር የታለመ የመሰለ ንግግር ማድረጓ ይታወቃል። ለዚህ ንግግራቸው የአማራ ፋኖ በጎንደር የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ አንተነህ ድረስ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል:_ 1) ፋኖ አገር አዳኝ እንጅ አገር አፍራሽ አይደለም’ ፋኖ ማለት አገር በተወረረ ጊዜ ክተት ብሎ ወገኑን ለማዳን መስዋእትነት የሚከፍል ህዝባዊ ሃይል ማለት ነዉ። 2) ፋኖ ማለት ልክ እንደ መይሳዉ አልገዛም ባይነትን የወገቡን ሽጉጥ በመጠጣት በተግባር የሚያሳይ ማለት ነዉ። 3) ፋኖ ማለት ልክ እንደ አፄ ምንሊክ ጥቁር ህዝቦችን ነፃ ማዉጣት ማለት ነዉ። 4) ፋኒት ማለት ልክ እንደ እትየ ጣይቱ ቆራጥ አመራርነት ማለት ነዉ። 5) ፋኖ ማለት በአምስት አመቱ የአርበኝነት ዘመን ወራሪን አይቀጡ ቅጣት የቀጣውን ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ማለት ነው። 6) የጦር ሚኒስትሩን አርበኛ ራስ አበበ አረጋይ ማለት ነው ፋኖ ማለት ‘የዶጋሊው’ ጀግና ራስ አሉላ አባ ነጋ ማለት ነው ፋኖ ማለት የአርበኛው ‘የገረሱ ዱኪ’ ወራሽ ማለት ነው። 7) ‘አለዉ አለዉና በማተቡ ፀና’ ተብሎ የተዘፈነለትንና በአርበኝነት ዘመኑ በእንግሊዞች ንገስ ተብሎ ንግስና የናቀዉን ራስ አሞራዉ ዉብነህና የጦር መሪዎችን ደጃች ብሬ ዘገየና አባተ አባ ሻንቆ ማለት ነዉ። 8 የራስ አሞራዉ ዉብነህ ቀኝ አዝማች የነበረዉና በ15 ዓመቱ በጀግንነቱ የታወቀዉን ሻለቃ በሪሁን ገብረየስ ማለት ነዉ። ፋኖ ማለት የቆላ ወገራዎቹን ምስጋናዉ በዜ፣ኪዳነማሪያም ገብረማሪያምና ክብሬ መለሰ ማለት ነዉ። 9) በጀግንነታቸዉ ኤርትራ ዉስጥ ትግል በመመስረት የኢትዮጵያን የአርበኝነት ታሪክ ያደሱትን የኢ/ያ ህዝብ አርበኞች ግንባር መስራቾችን አርበኛ ፍርዱ ልይህ፣አርበኛ አታለለ አሰፋ፣አርበኛ ጉበን ነጋሽ፣አርበኛ አስማማዉ ተዘራ፣ሻንበል ሙላዉ አለሙ፣አርበኛ መብራቱ ሲሳይና አርበኛ ጋራ ጉርባ ማለት ነዉ። 10) ከዉጭ አገር የሞቀ ኑሯቸዉን ትተዉ ወያኔን ለመፋለም ወደ ኤርትራ በርሃ አቅንተዉ መስዋእት የሆኑትን ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡና አርበኛ ተስፋ ላቀዉ ማለት ነዉ። 11) ሃብት ንብረቱን ትቶ እምብኝ ለወያኔ በማለት ለወልቃይትና ራያ ሲል መስዋእትነት የከፈለዉን አርበኛ ጎቤ መልኬ ማለት ነዉ። 12) በጠገዴ ወረዳ አመራ ቁስቋም በተባለ ቦታ ከወያኔ ጋር ተናንቀዉ የወደቁትን አርበኛ ማሃቤ በለጠ፣አርበኛ ሞላጃዉ ሙላዉ፣አርበኛ ቃቁ አወቀና አርበኛ ደሳለኝ አዱኛ ማለት ነዉ። 13) ሃምሌ 05/2008 ዓ.ም በመስዋእትነታቸዉ የአማራነትን ድባብ አስፈንጣቂዎችን አርበኛ ሲሳይ ታከለና አርበኛ ሰጠኝ ባብል ማለት ነዉ። 14) ከቅማንት ጽንፈኛ ጋር ተፋልመዉ በጀግንነት ያረፉትን አርበኛ ላመነዉ ታከለና አርበኛ ብርሌዉ ብቃለ ማለት ነዉ። 15) በ2009 ዓ.ም ወያኔን በመፋለም ተናንቆ የወደቀዉን መቶ አለቃ ደጀኔ መንግስቱ ማለት ነዉ። 16) የሃይማኖት ትምህርቱን በመተዉ ከልጅነት እድሜዉ ጀምሮ ወያኔን በመታገል ያሳለፈዉንና በጋይንት ደብረዘቢጥ ነሃሴ 05/2013 ዓ.ም መስዋእት የሆነዉን ዲያቆን ህርያቆስ አበበ ማለት ነዉ። 17) በቆላ ወገራ ቦዛ-ድምብልግሳ ያደራጀዉን ፋኖ በመምራት ከወያኔ ሰራዊት ጋር ፊት ለፊት በመፋለም የተሰዋዉን አርበኛ ያየሽ ማለት ነዉ። 18) በጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ሰሜን እዝ በተመታበት ጊዜ ወልቃይት ደጀና ተራራ ወያኔን በመፋለም መስዋእት የሆነዉን አርበኛ ጎይቶም ርስቀይ ማለት ነዉ። 19) በጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የባናት ምሽግ ሰባሪዉን አርበኛ ዘለቀ ዉቤ ማለት ነዉ። ፋኖ ማለት በጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሁመራ እስር ቤት ወያኔ ያሰራቸዉን ንጹህ አማራዎች ለማስፈታት የወደቀዉን ጀግና አርበኛ ሃይሌ ማሞ ማለት ነዉ። 20) በሃምሌ 16/2013 ዓ.ም በማይጸብሪ በማይላሃም ተራራና በቡያ ወንዝ የወደቁትን የጎንደር ፋኖዎች ፋኖ አዳነ፣ፋኖ ሃብቴና ፋኖ መስቀሌ ማለት ነዉ። 21) በጋይንት ደብረዘቢጥ በነሃሴ 05/2013 ዓ.ም በክብር በጀግንነት የተሰዋዉን አርበኛ ቻሌ እንየዉ ማለት ነዉ። ፋኖ ማለት በጭና ተ/ሃይማኖት ብና ስላሴ በተባለ ቦታ መስዋእት የሆነዉን ፋኖ ፋሲል ፈንቴ ማለት ነዉ። 22) በጨዉ በር ባቁሻ እየሱስ መስዋእት የሆኑትን ፋኖ ማሙየ ሞላና ፋኖ አበራ ማለት ነዉ። ፋኖ ማለት በወሎ ደሴ ከወያኔ ጋር በመፋለም መስዋእት የሆነዉን የራያዉ ተወላጅ ፋኖ ሞላ ደስየ ማለት ነዉ። 23) በጨዉ በር ባቁሻ እየሱስ የጀግና ሞት የሞተዉን አርበኛ ፍትጉ ማለት ነዉ። ፋኖ ማለት አማራዉ የገጠመዉ ፈተና የዛሬ 500 ዓመት ከገጠመዉ ፈተና ሁሉ ይበልጣል። 24) እኔም ፋኖ ነኝ በማለት ለወያኔና መሰል ፅንፈኞች መዳሃኒት በመሆን ለአማራነት ቤዛ ለኢትዮጵያዊነት ታሪክ የሆነዉን ጀነራል አሳምነዉ ፅጌ ማለት ነዉ። 25) ፋኖ ማለት የራያና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በህገ-መንግስቱ የሚፈታ ሳይሆን ከህገ-መንግስቱ በላይ በሆነ ፖለቲካዊ ዉይይት እና ታሪካዊ ሰነዶችና ማስረጃዎች መሆን ይጠበቅበታል በማለት የተናገሩትን ዶ/ር አምባቸዉ መኮነን ማለት ነዉ። የትኛው ነው ፅንፈኛ? የትኛው ነው በጥባጭ? ፋኖማ በዘመናት መካከል አገርን እያዳነ የመጣ የፅንፈኞችና የወራሪዎች መድሃኒት፣ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ደረጃ ከፍ ብሎ ሊቀነቀን የሚችል ስነ-ልቦና እንጅ በአምባገነኖች የፍረጃ ፖለቲካ የሚደናገጥና የሚወዛወዝ አይደለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply