You are currently viewing ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ በጎንደር 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ 4 ቀናት ሆኖታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ በጎንደር…

ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ በጎንደር 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ 4 ቀናት ሆኖታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ በጎንደር…

ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ በጎንደር 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ 4 ቀናት ሆኖታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ በጎንደር 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በሰዓት እላፊ ምክንያት የታሰረው ሚያዝያ 30/2014 መሆኑ ተገልጧል። ጉዳዩን ያጣሩ የአሚማ ምንጭ እንደሚሉት የሰዓት እላፊ አዋጅን ጥሳችኋል በሚል አብረው የተያዙም ሆነ ከእሱ በኋላ የታሰሩ 500 ብር ቅጣት እየከፈሉ እየወጡ ነው። ምንም የተለየ ወንጀል ባልፈጸመበት ለበርካታ ቀናት ያሳሰረው ሌላ ሳይሆን ፋኖነቱ እንደ ወንጀል በመቆጠሩ ነው ይላሉ የመረጃ ምንጫችን። ፋኖ ሰለሞን ቦጋለ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ብሎም ለኢትዮጵያ ከ6 ዓመታት በላይ በውጭ ሆኖ ስለመታገሉ፣ በትሕነግ ወረራ ወቅትም ከእግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ በመዝመት አማራን ብሎም ሀገርን ከታደጉ ጀግኖች አንዱ ስለመሆኑ መረጃዎች አመልክተዋል። “ለምን የአማራ ልዩ ሀይል ሽፍት አስፈለገው? ለአማራው የሚያስፈልገው አንድነት ነው” በሚል የሰሞኑን ግልጽነት የጎደለውን መንግስታዊ እንቅሰወቃሴ ይቃወም እንደነበር ተገልጧል። የዘርዐያቆብ አዝመራው ሻለቃ አዛዥ እና የጎንደር ከተማ ፋኖ ሰብሰቢ ፋኖ ሰለሞን አጠናውን በተመለከተም መሳሪያው ህጋዊ ስለሆነ እንዲመለስ የሚጠይቅ ደብዳቤ መጻፉንና ነገር ግን የጎንደር ከተማ ፖሊስ ይህ ጉዳይ የእኛ ጉዳይ አይደለም በማለቱ የሚቀበል መጥፋቱን ፋኖ ማቲዎስ መንግስቱ ተናግሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply