You are currently viewing “ፋኖ ሰለሞን አባተ ፣ፋኖ ጌታቸው ሙጨ እና ሌሎች የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላትን ከትላንቱ ያልተማረው ብአዴን አስሯቸዋል!”    የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ፋኖ ሰለሞን አባተ ፣ፋኖ ጌታቸው ሙጨ እና ሌሎች የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላትን ከትላንቱ ያልተማረው ብአዴን አስሯቸዋል!” የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ፋኖ ሰለሞን አባተ ፣ፋኖ ጌታቸው ሙጨ እና ሌሎች የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላትን ከትላንቱ ያልተማረው ብአዴን አስሯቸዋል!” የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጋሸና ግንባር አኩሪ ጀብድ የፈፀመው ፤የወያኔን በጣም ከባዱ ምሽግ የተባለውን አርቢት ምሽግ ለመደርመስ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ታሪክ የሰራውን ወንድማችን እና የላቀ አሰዋፅኦ አድርጎ ቆስሎ የተረፈው ጀግናው ፋኖ ሰለሞን አባተን ግንቦት 8/2014 አስረውታል። ለእስር የዳረገው ምክንያቱ ከወቅታዊ ጉዳይ አንፃር የሚል ተልካሻና እርባና ቢስ ምክንያት በማቅረብ ፤በስራ ላይ እያለ አፈነው ወስደውታል ። የአማራ ፋኖ በባህር ዳርም መንግስት በፋኖ አባሎቻችን ላይ እያደረገ ያለውን እስር ፣ወከባ እና እንግልት በአስቸኳይ እንዲያቆም መልዕክታችን እያስተላልፍን ። መላው የአማራ ፋኖ አባላት ፣መላው የባህር ዳር ከተማ ህዝብ እንዲሁም መላው የአማራ ህዝብ መንግስት እያደረገ ያለውን አፈና ፣ማዋከብ እና እስር በንቃት እንዲከታተል እና በቀጣይ ለምናደረገው ህዝባዊ ጥሪ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። በአፈና ፣በማዋከብ እና በእስር የሚቆም ምንም አይነት ትግል የለም። ላንጨርስ የጀመረነው ትግል አይኖርም! አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል! የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ግንቦት 08/2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply