ፋኖ ተኩሶ የማይስት አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት የሚያደርግ የነፍጠኞች የአብራክ ክፋይ ነው የፍኖ አባላት ኅዳር 30/2014/አሻራ ሚዲያ/ ጠላት ለሽብር የተፍረከረከ ክንዱን ሲጠቀም የጠላት…

ፋኖ ተኩሶ የማይስት አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት የሚያደርግ የነፍጠኞች የአብራክ ክፋይ ነው የፍኖ አባላት ኅዳር 30/2014/አሻራ ሚዲያ/ ጠላት ለሽብር የተፍረከረከ ክንዱን ሲጠቀም የጠላትን ክንዶች ለማንደድ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ የአማራ ሚሊሻ እና ፋኖ ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ ስነልቦናና ኀያል በሆነ ክንዳቸው ለሀገርና ለህዝብ እየተዋደቁ ይገኛሉ። አማራን ዝቅ ለማድረግ እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጣውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በቆፈረው ጉድጓድ ለመቅበር በጋሸና ግንባር ከመከላከያ፣ ከአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ ጋር ተሰልፈናል የሚለው ፋኖ ውብአንተ አባተ(ገብርዬ) የጎንደር ፋኖ ገብርዬ ሻለቃ አዛዥ ነው። ፋኖ ተኩሶ የማይስት አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት የሚያደርግ የነፍጠኞች የአብራክ ክፋይ ነው ያለው ፋኖ ውብአንተ (ገብርዬ) ይሄን አረመኔ ቡድን በወረራቸው የአማራ መሬቶች ላይ ለመቅበር እስከ ህይወት መስዕዋትነት እየከፈልነ በግንባር ተሰልፈናል ብሏል። ፋኖ መቶ አለቃ አበራ አጉማስ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት ባልደረባ አሁን ደግሞ የአማራ ፋኖ በባህርዳር የሻለቃ አዛዥ ሲሆን የህወሓት ወረራ በአማራ ህዝብ ህልውና የመጣ ስለሆነ እንደ አማራ አንድ በመሆን ወንበዴውን ቡድን በጋሸና ግንባር እየቀጣነው እንገኛለን ብሏል። ህወሓት ለብዙ ዓመታት ኢትዮጵያን ሲመራ ኖሯል አሁን ግን በርካሽ አላማው ምክንያት ከስልጣን ተወግዷል ያለው ፋኖ መቶ አለቃ አበራ አጉማስ ኢትዮጵያን ብሎም አማራን ለማጥፋት የጀመረውን ወረራ ለመቀልበስ ፋኖ በተለያዩ ግንባሮች የህይወት መስዕዋትነት እየከፈለ እና እየተዋደቀ ይገኛል ብሏል። የታገልንለትን አላማ ወደጎን በመተው የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ ኖረው በህዝብ እምቢተኝነት ቢወገዱም አሁን ላይ አብሯቸው ታግሎ ስልጣን ያስያዛቸውን የአማራ ህዝብ መልሰው እየወጉት ይገኛሉ። እኛ ግን ለዳግም ውርደት ስላልተዘጋጀን ወራሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን እስከ መጨረሻው እንፋለመዋለን ድልም እናደርጋለን ሲሉ የፋኖ አባላቱ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply